ወደ ኢትዮጵያ እየሄዱ ከነበሩ አምስት አንድ የቤተሰብ አባላት የያዙትን ገንዘብ ትክክለኛ መጠን ባለማሳወቃቸው ላይ የዋሽንግተን ደለስ አየር ማረፊያ ድንበር ጠባቂ ሰራተኞች 27,330 ዶላር እንደተያዘ ተዘግቧል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊና በዜግነት አሜሪካዊ የሆነው አባት 8000 ዶላር ብቻ እንደያዘ ያሳወቀ ሲሆን የሴኩሪቲ ሰራተኞች ትክክለኝውን መጠን በፅሁፍ እንዲያስቀምጥ ሲጠይቁት ልጅየው ሌላ 8000 በጠቅላላው 16000 ዶላር እንዳለው ተናገረ።
የሴኩሪቲ ሰራተኞች ኬሪኦን ሻንጣቸውን ሲፈትሹ ተጨማሪ 11000 ዶላር አግኝተዋል። የሴኩሪቲ ሰራትኞች በጠቅላላው 27330 ዶላር የወረሱ ሲሆን 830 ዶላር ብቻ መልሰውላቸዋል። ሆኖም አውሮፕላናቸው ጥሏቸው በመሄዱ በረራቸው ተስተጓጉሏል። ተጓዦቹ በወንጀል ክስ ስላልቀረበባቸው ስማቸው እንደማይለቀቅ በደረ-ገጻቸው ትላንት ማክሰኞ 07/12/2022 አስታውቀዋል።
ዜናውን ያገኘነው ከ Customs and Border Protection ድረ-ገጽ ነው።