ባለፈው ሳምንት ጁላይ 6 ፖሊስ የስልክ ጥሪ ይደርሰዋል። ደዋዩ 6800 eastern avenue ብሎክ ላይ ከመኪናው ንብረት እንደጠፋው ይናገራል። ፖሊስ በቦታው ደርሶ ባደረገው ምርመራ የደዋዩ መኪና የነዳጅ ታንከር ማንነቱ ባልታወቀ ሰው ጠዋት 11፡40 አካባቢ በድሪል ተበስቶ ነዳጁ መሉ በሙሉ እንደተወሰደ ተደርሶበታል። የታኮማ ፓርክ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ መረጃ ያለው ማንኛውም ሰው በስልክ ቁጥር 301-270-1100 ጥቆማ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።