12/12/2024
Copy of Rent car instagram post

የሞንጎምሪ ካውንቲ ከየትኛውም ቦታ የህዝብ ትራንስፖርት/ባይስክል/ የጋራ ቫን ሰርቪስ ተጠቅመው መተው በካውንቲው ለሚሰሩ ሰራተኞች ታክስ የማይከፈልበት በወር እስከ 280$ ድረስ ድጎማ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ይህ አዲስ ፕሮግራም በዋናነት ቀጣሪዎች ለተቀጣሪዎቻቸው የትራንስፖርት አበል/ድጎማ እንዲያደርጉ የሚያበረታታ ፕሮግራም ነው።
ቀጣሪዎች በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ ከሆኑ ለሰራተኞቻቸው በወር ከ25$ ጀምሮ እስከ 280$ ድረስ በአመት ደሞ እስከ 40000$ ድረስ የትራንስፖርት ክፍያ ካደረጉ የካውንቲው መንግስት 75% ያህሉን እንደሚከፍል አስታውቋል። በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን በካውንቲው እስከሰሩ ድረስ ነዋሪ መሆን ግዴታ አይደለም።
ተቀጣሪዎች የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን ከቀጣሪዎቻቸው ጋር መማከር ይችላሉ። መሉ መረጃው ሊንኩን ተከትለው ይሂዱ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት