12/12/2024
ምስል ከ @dcfireems የትዊተር ገፅ

ምስል ከ @dcfireems የትዊተር ገፅ

ዛሬ ሐሙስ ምሽት ዋይት ኃውስ ፊትለፊት በሚገኘው የላፋያት መናፈሻ የወደቀ መብረቅ በ2 አዋቂ ወንዶችና በ2 አዋቂ ሴቶች ላይ ከባድ ጉዳት እንዳደረሰ የዲሲ የእሳትና አደጋዎች ተከላካይ ድርጅት አስታወቀ።

በመብረቅ የተመቱት ግለሰቦች አደጋው ለህይወታቸው እንደሚያሰጋቸውና ወደሆስፒታል ለተጨማሪ እርዳታ እንደሄዱ ታውቋል።

ፖሊስ ከምሽቱ 8፡30 ላይ በአደጋው ዙሪያ መግለጫ ለመስጠት ቀጠሮ ይዟል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት