የዘር እኩልነትና የማህበራዊ ፍትህ ዳሰሳ
ትራይቭ ሞንጎምሪ 2050 (ትራይቭ 2050) በሞንጎምሪ ካውንቲ ፕላኒንግ ዲፓርትመንት ተዘጋጅቶ የቀረበ አዲስ ካውንቲ አቀፍ አጠቃላይ እቅድ ነው። ትራይቭ 2050 ለቀጣይ 30 አመታት የካውንቲውን የወደፊት እድገትና ልማት ለመወሰንና ለመምራት የሚያገለግል የፖሊሲ ሰነድ ነው። ይህ ትራይቭ 2050 የተሰኘ የፖሊሲ ሰነድ የሞንጎምሪ ካውንቲን የወደፊት የመሬት አጠቃቀም፤ ትራንስፖርት፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል።
ይህ ፕሮጀክት በታሪክ ለተጎዱና ለችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የማህበረብ አካላት በትራይቭ 2050 ዕቅድ ውስጥ በተገቢውና በትክክለኛው መንገድ እንዲወከሉ ያለመ ፕሮጀክት ነው። ይህ ፕሮጀክት ከማህበረሰቡ የሚያገኘውን ግብረ መልስ እንደ ግብዓት በመጠቀም አሁን ያለውን የፕላን ሂደት ጠንካራና ደካማ ጎኖች ይዳስሳል። በዚህ ላይ ተንተርሶም ትራይቭ 2050ን ለማሻሻልና ማእከላዊ አጀንዳ የሆኑትን የዘር ፍትኃዊነትና ማህበራዊ ፍትህን በዋነኛ የእቅዱ ምሰሶዎች በማካተት የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣል።
ሊሰሩ የታቀዱ ተግባራት፡
- የካውንቲውን ጥቁሮች፤ ቀደምት ነዋሪዎች (Indigenous)፤ ሌላ ቀለም ያላቸው ሰዎች People of Color (BIPOC)ና አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች ተደራሽ ያደረገ ጥናት
- በካውንቲው በሙሉ ያሉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትንና የተመረጡ የማህበረሰቡ ተወካዮችን ማሳተፍ
- አጠቃላይ የማህበረሰብ መድረኮችንና ውይይቶችን በማዘጋጀት፤ የአነስተኛ ቡድኖች ጥናት በማካሄድ፤ በመጠይቅ የታገዙ የዳሰሳ ጥናቶችን በማድረግ ግብዓቶችን መሰብሰብ
- በካውንቲው ጥቁሮች፤ ቀደምት ነዋሪዎች (Indigenous)፤ ሌላ ቀለም ያላቸው ሰዎች People of Color (BIPOC)ና አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎች ላይ በተሰሩ ጥናቶችና ውይይቶች እንዲሁም በተሰበሰቡ ግብዓቶች መሰረት ትራይቭ 2050 የዘርና የማህበራዊ ፍትህን በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲተገበር የመፍትሄ አቅጣጫ ያቀርባል።
- ቀደምትና አሁንም ያሉ የዘርና ማህበራዊ ፍትኃዊነት ጉዳዮችን የሚያካትት አዲስ ምዕራፍ በትራይቭ 2050 ሰነድ ውስጥ ማካተት።
እርስዎም የሞንጎምሪ ካውንቲ ነዋሪ ከሆኑ ይህንን መጠይቅ ዛሬውኑ ይሙሉና ድምጽዎን ያሰሙ። መጠይቁን በእንግሊዝኛ ለመሙላት ይህን ይጫኑ።