12/12/2024
Image Source https://twitter.com/iamwesmoore

Image Source https://twitter.com/iamwesmoore

በመጀመሪያ የሙሉ ቀን ስራቸው ገዢ ዌስ ሙር በቀድሞው ባለስልጣን ታግዶ የነበረን 69 ሚልየን ዶላር በማስለቀቅ ለሜሪላንድ መንግስት ቅድሚያ እሰጣቸዋለው ላላቸው ጉዳዮች እንዲውሉ ተመድበዋል። በተጨማሪም አዲስ የመንግስት ተቋም እንዲቋቋም የሚፈቅድ ማዘዣ አውጥተዋል። በአዲሱ ማዘዣ መሰረትም የሜሪላንድ አገልግሎትና የዜጎች ኢኖቬሽን ዲፓርትመንት ተቋቁሟል። በቀጣይ ሳምንታትም አስተዳዳሪ እንደሚሾምለት ተናግረዋል።

ይህንንና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክተው ዛሬ ሐሙስ 01/19 ከምክትላቸው አሩና ሚለር ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል። ዛሬ ይፋ በተደረገ የበጀት ድልድል እንደታየው 69 ሚልየን ዶላሩ እንደሚከተለው ተከፋፍሏል።

ናቸው ተብሏል።

ምክትል ገዢ አሩና ሚለር አክለው ለአዕምሮ ደህንነትና ጤና የተለየ ትኩረት በማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ዌስ ሙር በትላንትናው ዕለት ለሜሪላንድ የመጀመሪያው ጥቁር ገዢ ሆነው መሾማቸው ይታዋቃል። በአሁኑ ሰዓትም በመላው አሜሪካ ግዛቶች ብቸኛው ጥቁር የክልል ገዥ ናቸው። ምክትላቸው አሩና ሚለርም በሜሪላንድ ታሪክ የመጀመሪያዋ የኢንዲያ-አሜሪካን ደም ያላቸው ምክትል ገዢ ናቸው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት