12/12/2024
story-1

እየተባባሰ የመጣውን የኦፒዮይድ ኦቨርዶዝን በማስመልከት ዛሬ የሞንጎምሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክናይት ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር በመሆን ከጊዜ ወዲህ እያሻቀበ የመጣውን የድራግ ኦቨርዶዝ በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል።

Image Source @MCPSTV

በመግለጫው ላይ ዶ/ር ሞኒፋ እንዳሉት የሟቾች ቁጥር በ2022 በ120% አሻቅቧል። ዶ/ሞኒፋ አክለውም ማንኛውም ወላጅ የኔ ልጅ ጨዋ ነው፤ ይኼ ጉዳይ እኔን አይመለከትም ከሚል አስተሳሰብ ወቶ ከልጆቹ ጋር ስለ ፌንታኒል መወያየት እንደሚገባው ተናግረዋል።

Image Source @MCPSTV

በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የካውንቲው የፖሊስ አለቃ፤ የካውንስል አባላት፤ በተለያየ ኃላፊነት ላይ ያሉ የህዝብ ትምህርት ቤት ሰራተኞች፤ የጤና ባለሞያዎችና ይህግ አካላት ተገኝተውበታል።

በቀጣይም ስለዚህ ገዳይ መድሃኒት አደገኛነት ለመወያየት Montgomery Goes Purple ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጋር በመተባበር በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ቤተሰቦች ቅዳሜ፣ ጃንዋሪ 28 እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

በመድረኩ ውይይት የሚያቀርቡት ባለሙያዎች ስለ ፌንታኒል (fentanyl) አደገኛነት እና ስርጭት፣ ለተማሪዎች የመከላከያ መሳሪያዎች እና የመከላከል ሁኔታዎች፣ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለህክምና ግብዓቶች ጠቃሚ መረጃዎችን ይሰጣሉ። ዝግጅቱ ክላርክስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ 9:30 a.m.–11:30 a.m. ይካሄዳል። አድራሻው፦ Clarksburg High School cafeteria, 22500 Wims Road in Clarksburg

በተጨማሪም ዝግጅቱ MCPS ዋናው ገጽ (MCPS homepage) ላይ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት