12/12/2024
We are proud of you

የዲሲ መንግስት ከክልሌ ውጪ ያሉ ባለመኪኖችን በወር ከሁለት ጊዜ በላይ በከተማው ከታዩ በዲሲ ዲኤምቪ የመኪና ምዝገባ ማድረግ አለባቸው ብሏል፡፡ ይህንንም ለማስፈጸም የዲሲ ዲፓርትመንት ኦፍ ፐብሊክ ወርክስ/ዲፒደብሊው/ የቁጥጥር ስራ ጀምሯል ብሏል፡፡ በዚህም መሰረት ዲፒደብሊው አንድ የዲሲ ታርጋ ያልለጠፈ መኪና በ30 ቀን ውስጥ ለ2 ጊዜ ካገኘ የማስጠንቀቂያ ትኬት የሚልክለት ሲሆን የመኪናው ባለቤት መኪናውን በዲሲ ዲኤምቪ ካላስመዘገበና በከተማው መኪናው ድጋሚ ከተገኘ የትራፊክ ቅጣት ወይንም መኪናው ቶው ይደረጋል ተብሏል፡፡

እንደ ሜሪላንድና ቨርጂኛ ካሉ ከሌላ ስቴት አዘውትረው ወደ ዲሲ የሚገቡ ሰዎች የሮዛ ዌይቨር (Registration of Out-of-State Automobiles (ROSA)) በኦንላየን፤ በአካል ወይንም በፖስታ ቤት መጠየቅ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ ይህን ዌይቨር ለመጠየቅ የሚከተሉት ዶክመንቶች ያስፈልጋሉ፡፡

  • A copy of the DPW citation or warning notice issued to the vehicle in question
  • Your original lease, deed, or mortgage statement for your out-of-District residence
  • A current utility bill (issued within 60 calendar days) at your out-of-District residence
  • Your valid registration card for the vehicle in question

If you reside with someone and the lease, deed, or mortgage statement is not in your name, you must provide all of the following as proof of non-District residency:

  • A copy of the warning notice issued to the vehicle in question
  • A statement from the individual you reside with attesting to the fact that you reside at that individual’s home
  • A copy of the individual’s original lease, deed, or mortgage statement
  • A copy of the individual’s current utility bill (issued within 60 calendar days)
  • Your valid vehicle registration card for the vehicle in question. The registration card must reflect the same address that is on the individual’s original lease, deed, or mortgage statement, and utility bill.

በኦንላየን ለማመልከት ይህን ይጫኑ

በፖስታ ቤት ለማመልከት የሚከተለውን አድራሻ ይጠቀሙ

DC DMV
Attn: ROSA Exemption
PO Box 90120
Washington, DC 20090 

የዚህ ፕሮግራም ምዝገባ ለአንድ አመት ብቻ ነው የሚጸናው፡፡ ምዝገባውን በየዓመቱ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡ ይህ ምዝገባ የፓርኪንግ ፍቃድ እንዳልሆነና በየመንገዱ ያሉ የፓርኪንግ ህጎች በማንኛውም መኪና ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆኑ አክለው ገልጸዋል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት