12/12/2024
We are proud of you (2)

ነገ ማክሰኞ ጁን 27ና ከነገወዲያ ረቡዕ ጁን 28፣ 2023 ይኖራል በተባለ የፊልም ቀረጻ ምክንያት በዳውንታውን ዲሲ አካባቢ ያሉ አንዳንድ መንገዶች እንደሚዘጉ የዲሲ መንግስት ቢሮ አስታውቋል። በነዚህ ሁለት ቀናት ከስር በተዘረዘሩት ቦታዎች መኪና ማቆም የሚከለክሉ ምልክቶች የሚለጠፉ ሲሆን በተወሰኑት በተወሰኑት ደግሞ መኪናዎች እንዳያልፉ የሚያግዹ ጊዜያዊ አጥሮች እንደሚደረግባቸው ተነግሯል።

መግለጫው የፊልሙ ምንነትም ሆን አይነት አልተጠቀሰም።

እስከ አርብ ጁን 30 2023 7፡00ፒኤም ለመኪና ማቆሚያ የሚከለከሉ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው።

  • 15th Street from G Street to Constitution Avenue, NW
  • F Street from 14th Street to 15th Street, NW
  • Upper Pennsylvania Avenue from 14th Street to 15th Street, NW
    Lower Pennsylvania Avenue from 14th Street to 15th Street, NW

የሚከተሉት መንገዶች ደሞ ለማንኝውም መኪና ከማክሰኝ ጁን 27 2023 6፡30ፒኤም ጀምሮ እስከ ረቡዕ ጁን 28፤ 2023 6ኤኤም ድረስ እንዲሁም ከረቡዕ ጁን28 6፡30 ፒኤም እስክ ሐሙስ ጁን 29 2023 6፡00ኤኤም ድረስ ይዘጋሉ ተብሏል።

  • 15th Street from G Street to Constitution Avenue, NW
  • F Street from 14th Street to 15th Street, NW
  • Upper Pennsylvania Avenue from 14th Street to 15th Street, NW
  • Lower Pennsylvania Avenue from 14th Street to 15th Street, NW

ተጨማሪ መረጃ: የፊልም ቀረፃው ባለቤት ማርቭል ስቱዲዮ እንደሆነና የማርቭል መኪኖች በቦታው እንደቆሙ ታውቋል

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት