F2DSmMkaAAE3znv

ሞንጎምሪ ካውንቲ የትራፊክ ፖሊስ ዲፓርትመንት እኚህን አዲስ የፖሊስ መኪኖ ዛሬ ወደስራ እንደሚያስገባቸው አስተዋውቋል። ይህ አዲስ የፖሊስ መኪና ፅሁፉ እንዳይታወቅ ሆነ ተብሎ እንደነጠላ ባለ ልጥፍ የተሸፈነ ሲሆን የዚህ ምክንያት ደሞ ሰዎች የፖሊስ መኪና እንደሆን እንዳያውቁትና አጥፊዎችን እጅ ከፍንጅ ለመያዝ ነው ተብሏል። በዋናነትም ከፍጥነት በላይ የሚያሽከረክሩ፤ ያለ ሲትቤልት የሚያሽከረክሩ፤ ጠጥተው የሚያሽከረክሩ በሞገድ የሚያሽከረክሩና እየነዲ ስልካቸውን የሚጎረጉሩ አሽከርካሪዎችን ለመቀነስ ይረዳል ተብሏል።

እነዚህ አዳዲስ መኪኖች ከሌላው የፖሊስ መኪና ጋር ተመሳሳይ ፅሁፍ ቢኖራቸውም ሆነ ተብሎ በነጭና ግራጫ ቀለም ተሸፍኗል። እነዚህ መኪኖች ከዛሬ ሐሙስ ጁላይ 27 2023 ጀምሮ ወደስራ እንደሚገቡና ሙሉ የፖሊስ ዩኒፎርም ባደረጉ የካውንቲው የትራፊክ ፖሊሶች እንደሚነዱ የካውንቲው ፕሬስ ሪሊዝ ላይ ተነግሯል።


ስለዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘትና የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣ በኢሜይልዎ እንዲደርስዎት ከስር ያለውን ተጭነው ይመዝገቡ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.