የኸንዴይ መኪኖች ዝርፊያን ተከትሎ የዲሲ ከንቲባ ቢሮ ከዲሲ ፖሊስና ከኸንዴይ (Hyundai) ጋር በመተባበር ለተመረጡ የኸንዴይ(Hyundai) መኪና ሞዴሎች የደህንነት ሶፍትዌር ገጠማ ፕሮግራም አዘጋጅቷል። ይህ አገልግሎት ለማንኛውም ባለ ኸንዴይ(Hyundai) መኪና ባለቤት በነጻ ይሰጣል። ማንኛውም ከስር ያሉት የኸንዴይ(Hyundai) መኪና ሞዴሎች ባለቤት ከዛሬ ጁላይ 27 ጀምሮ እስከ ጁላይ 31 2023 ድረስ በ2500 Independence Ave SE በሚገኘው የአር.ኤፍ.ኬ ስቴዲየም ፓርኪንግ ሎት 8 ከጠዋቱ 8ሰዓት እስከ ምሽት 7ሰዓት በመሄድ የነጻ አገልግሎት ማግኘት ይችላል። የሜሪላንድም የቨርጂንያም ነዋሪ የሆነና የኸንዴ መኪና ያለው ሰው በዚህ ፕሮግራም መጠቀም ይችላል።
የዚህ ሶፍትዌር ገጠማፕሮግራም ላይ መሳተፍ የሚችሉት የኸንዴይ መኪና ሞዴሎች ከስር በምስሉ ላይ ተቀምጠዋል።
ስለዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘትና የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣ በኢሜይልዎ እንዲደርስዎት ከስር ያለውን ተጭነው ይመዝገቡ