የሊሞ ሹፌር የሆነው ሚካኤል ጽጌ ድብደባና ዝርፊያ በዲሲ
ምስል ከፌርፋክስ ፖሊስ

የፌርፋክስ ፖሊስ እንዳሳወቀው በጁላይ 16 ለሊት 4 ሰዓት አካባቢ 5820 ሴሚናሪ ሮድ ላይ በሚገኘው የላየንስ ዴን ላውንጅ ወደ መሬት በተተኮሰ ጥይት 2 ሴቶች ላይ በጥይቱ ፍንጥርጣሪ ጉዳት ደርሶባቸው ነበር፡፡ ይህን ተከትሎም ለደረሰባቸው ቀላል ጉዳት በአካባቢው ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተዋል፡፡

ምስል ከፌርፋክስ ፖሊስ

ምስል ከፌርፋክስ ፖሊስ

ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ታዲያ የዚህ ወንጀል ፈጻሚ ነው ያለውን የ25 ዓመት ወጣት አብዱልከሪም ሃሊድ በተጠርጣሪነት ፈርጆ ቢፈልገው በሰዓቱ ከቦታው መሰወሩን አስታውቆ ነበር፡፡ ይህንን ተከትሎም መርማሪዎች የእስር ማዘዣ አውጥተው አብዱልከሪምን ሲያፈላልጉ የቆዩ ሲሆን ትላንት በአሌክሳንድሪያ ከተማ አብዱልከሪም እንደተያዘ አስታውቀዋል፡፡

በዚህ ወንጀል ተጨማሪ መረጃ ያላቸው በስልክ ቁጥር 703-256-8035 ደውለው እንዲጠቁሙ ጠይቀዋል፡፡

መረጃውን ያገኘነው ከፌርፋክስ ፖሊስ ነው። የፖሊስን መረጃ ለማየት ይህን ሊንክ ተከትለው ይሂዱ።


ስለዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘትና የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣ በኢሜይልዎ እንዲደርስዎት ከስር ያለውን ተጭነው ይመዝገቡ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.