እንደሚኖሩበት ስቴት ለመንግስት በታክስና በመሳሰሉት እላፊ ከፍለው ወይንም የመንግስት ተቋማት በስህተት እላፊ አስከፍለዎት ከሆነ እንዴት ነው ቀሪ ገንዘብዎን መውሰድ የሚችሉት? እንደሚኖሩበት ወይንም እንደሚነግዱበት ስቴት አንዱን ሊንክ ተጭነው መረጃዎትን በማስገባት በምስሉ ላይ እንደሚታየው በስምዎት መንግስት ጋር የቀረ ንብረት ካለዎት ይመለስልኝ ብለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የዲሲ መንግስት ብቻ በ2022 የበጀት አመት ብቻ $27,204,494.87 ለትክክለኛ ባለቤቶቹ መልሷል፡፡ የቨርጂንያ መንግስትም ከአንድ ቢልየን ብር ተመላሽ እንዳደረገ በድረገጹ ላይ አሳውቋል፡፡
ምስል የኢትዮጲክ ባልደረቦች በምሳሌነት በዲሲ የራሳቸውን ስም አስገብተው ንብረት እንዳላቸውና እንደሌላቸው ሲያረጋግጡ የተነሳ ስክሪንሻት ነው፡፡
ስለዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘትና የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣን ለማንበብ ከስር ያለውን ተጭነው ይመዝገቡ