12/12/2024
297710705_184463597319359_3502591650101770768_n

UPDATE 08/07/2023—– በዚህ ውድድር የተጠቆሙትና ለመጨረሻው ዙር ውድድር የቀረቡት የምግብና የመጠጥ ቤቶች ዝርዝር ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡ የ WTOP አድማጮችና አንባቢዎችም ምርጥ የሚሏቸውን የምግብና መጠጥ ቤቶች እንዲመርጡ ዛሬ የመምረጫ ገጹን ከፍቷል፡፡ በዚህ የመጨረሻ ዙር ተሳታፊዎች ዝርዝር ውስጥ ታዲያ የኛዎቹ ላንጋኖ ሬስቶራንትና ሻላ ሬስቶራንት በምርጥ ኢንተርናሽናል ምድብ ተካተዋል፡፡ በምርጥ ቡናና ቁርስ ቤቶች ዝርዝር ውስጥ ደሞ ከፋ ኮፊ (ዊተን ላይብረሪ)፤ ቡና ኮፊ ኃውስ፤ አዱሊስ ኮፊ ኤንድ ሮስትሪና ሲዳሞ ኮፊ ተካተዋል፡፡ በየዘርፉ አሸናፊዎች 1000$ ያገኛሉ፡፡ ይገባቸዋል የምትሏቸውን ለመምረጥ ይህን ሊንክ ተጭነው ይሂዱ፡፡


አምና በዚህ ውድድር አንድ እንኳን የኢትዮጵያ ሬስቶራንት አልተጠቀሰም። እኛም በደንፉ ለምን ብለን ስንጠይቅ ጠቁሙ ስትባሉ ለምን አልጠቆማችኋቸውም ብለው መልሰውልናል። ያው የራሳችን ድክመት ነው ማለት ነው። ዘንድሮ ድክመታችንን አሻሽለን ቢያንስ 3 የኢትዮጵያ ምግብ ቤቶችና ቡና መሸጫዎች እንዲያሸንፉ ማረግ አለብን። ይህ የሁላችንም ኃላፊነት ነው!!!

በአመታዊው የ WTOP News ምርጥ 10 ምግብ ቤቶች ውድድር ላይ የኢትዮጵያውያንን ምግብ ቤቶችና ቡና መሸጫዎችን ይጠቁሙና አሸንፈው 1000$ እንዲወስዱ አግዟቸው። የጥቆማ ማመልከቻው አሁን ተከፍቷል እስከ ጁላይ 28ም ክፍት ሆኖ ይቆያል። አሪፍ ነው የምትሉትን ምግብ ቤት ወይንም የቡና መሸጫ በየዘርፉ መጠቆም ትችላላችሁ። ከአንድ ጊዜ በላይ መጠቆም ይቻላል። ይገባቸዋል የምትሏቸውን ምግብ ቤቶች ከስር ያለውን ሊንክ በመከተል ጠቁሙ።

የአንደኛችን መሻሻል የሁላችንም መሻሻል ነው። የአንዳችን ስኬት ለሁላችንም ነው። እንዲህ አይነት አጋጣሚዎች ሲያመልጡን ደሞ መቆጨት አለብን። ለምን ብለን እንጠይቅ። እንዴት እናሻሽል ብለን እንጠይቅ። ብቻችሁን አደላችሁም። የምናግዛችሁ ነገር ካለ እኛን ጠይቁን። ወደድንም ጠላንም በማህበር ሁላችንንም ኢትዮጵያውያን ተብለን ነው እዚህ የምጠራው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት