የፍራንኮንያ ፖሊስ ጣቢያ መርማሪዎች እንዳሳወቁት ትላንት 07/18/2023 ከምሽቱ 10፡51 ላይ በJeff Todd Way and Telegraph Road in Fort Belvoir መንገድ መጋጠሚያ ላይ ያጋጠመ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት እንደቀጠፈ አስታውቀዋል።
እንደመርማሪዎቹ ከሆነ የ2014 ካዲላክ ይነዱ የነበሩት ሹፌር መንዳት ከነበረባቸው በተቃራኒ የመንገዱን ግራ ይዞ በሚነዳበት ጄፍ ቶድ ዌይ መንገድ ላይ ቴሌግራፍ ሊደርሱ ሲቃረቡ ከፊት መንገዱን ጠብቆ ከሚመጣ የ2001 ኒሳን ፓዝፋይንደር መኪና ጋር ተጋጭቷል።
ፖሊስ የካዲላክ መኪናው ሹፌር ማህደር ፋሲል የተባለ/ች የ27 ዓመት ወጣት (ፖሊስ ፆታቸውን ይፋ አላደረገም) እንደሆነ/ችና ከአደጋው በኋላ ወደሆስፒታል የተወሰዱ ቢሆንም እንደደረሱ ህይወታቸው እንዳለፈ ተጠቁሟል። የኒሳኑ ሺፌርም ከባድ ጉዳት ደርሶበት ወደሆስፒታል ተወስዶ ህክምና እየተደረገለት እንደሚገኝ ተነግሯል።
የፖሊስ መርማሪዎች በአደጋው ላይ መረጃ ያለው ሰው በስልክ ቁጥር 703-280-0543 ደውለው እንዲጠቁሙ ጠይቀዋል።
ለጥቆማው ብሩክንና መረጃ በማስተካከል ያገዘችንን ሳባ ተፈራን እናመሰግናለን