12/12/2024
የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የላላ ብሎን አላቸው ተባለ

የአሶሼትድ ፕሬስ ዛሬ ዲሴምበር 29 2023 እንደዘገበው የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች የላላ ብሎን እንዳላቸውና ይህ አውሮፕላን ያላቸው የአየር መንገዶች ይህንን ወሳኝ የብሎን ማጥበቅ እንዲያደርጉ አስጠንቅቋል። እስካሁን በዚህ ምክንያት የደረሰ አደጋ እንደሌለ ቦይንግ ያሳወቀ ሲሆን የአሜሪካ ፌደራል አቪየሽን አድሚንስትሬሽን ይህንን ተከትሎ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ አሳውቋል።

በአሜሪካ ውስጥ ይህ አውሮፕላን ያላቸው የአየር መንገዶች ዩናይትድ፤ አሜሪካን፤ ሳውዝ ዌስትና አላስካ ሲሆኑ ማንኛቸውም የበረራ መስተጓጎል እንደማይገጥማቸው ለአሶሼትድ ፕሬስ አሳውቀዋል። እንደቦይንግ ገለጻ ከሆነ ይህንን የላላ ብሎን ለማጥበቅ ከ2 ሰዓት በላይ እንደማይፈጅ አሳውቀዋል።

ከዚህ ቀደም ይህ የቦይንግ 737ማክስ አውሮፕላን የኢንዶኔዥያና ኢትዮጲያ አኤርላየንስን ጨምሮ በደረሰው አደጋ ምክንያት በአለም አቀፍ ደረጃ እንዳይበሩ ለ20 ወራት ታግደው እንደነበር ይታወቃል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት