የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ዛሬ 7/30 እንዳሳወቀው ባሳለፍነው ቅዳሜ ጁላይ 27 ምሽት 8:59 ገደማ በላንግሌይ ድራይቭና ዩኒቨርስቲ ቡሌቫርድ ላይ መንገድ የሚያቋርጥ እግረኛ እንደተገጨ ለፖሊስ ይደወላል::
በሰአቱ በቦታው የተገኘው ፖሊስም የተገጨው ሰው እዛው ለህልፈት እንደተዳረ ተገንዝበዋል::
እንደ ፖሊስ ሪፖርት ሟች የተገጨው በሰማያዊ የ2020 ጂፕ ግራንድ ቸሪኪ ሲሆን የሟችን ማንነትም ዛሬ ይፋ አድርጏል:: ሟችም የ30 አመት ወጣት የሆነው አማን አብርሀም ገብረየሱስ እንደሆነ ታውቋል::
ፖሊስ ይህ እስካሁን በምርመራ ላይ እንዳለና ግችቱን ያየ ወይም በቦታው የነበረ ሰው በስልክ ቁጥር 240-773-6620 ደውሎ ለምስክርነት እንዲቀርብ ጠይቋል::
አደጋውን ያደረሰው አሽከርካሪ በቦታው ሆኖ ፖሊስ እስከሚመጣ እንደጠበቀም ፖሊስ አስታውቋል::
ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን::