12/12/2024
የሊሞ ሹፌር የሆነው ሚካኤል ጽጌ ድብደባና ዝርፊያ በዲሲ (21)

ትላንት ቅዳሜ ጌቲስበርግ አካባቢ በነበረው የኢትዮጵያውያን ኮሚውኒቲ ፒክኒክ ላይ ፋውዛን ሀሰን የተባለ የ6 ዓመት ታዳጊ መጥፋቱንና ፖሊስ የጠፋውን ህጻን አፋልጉኝ ብሎ ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር። ህጻን ፋውዛን ሀሰን መናገር የማይችልና ከኦቲዝም ጋር የሚኖር ታዳጊ እንደሆነ የፖሊስ ሪፖርት ላይ ተጨምሮ ተገልጿል።

ፖሊስ ታዲያ ዛሬ እሁድ የትላንቱ ፒክኒክ ከተካሄደበትና ፋውዛን ጠፍቶበታል በተባለው አካባቢ በ50 ሜትር አቅራቢያ በሚገኘው ኩሬ ውስጥ የሰጠመ ሬሳ ማግኘቱን አስታውቋል።
ፖሊስ የተገኘው ሬሳ የፋውዛን እንደሆነ ባደረገው የፕሬስ ኮንፈረንስ አስታውቋል።

ፖሊስ ለወላጆች መርዶውን እንዳሳወቀም የፖሊስ ባልደረባዋ ተናግረዋል::

የኢትዮጲክ ባልደረቦች ለወላጆችና ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት