የሊሞ ሹፌር የሆነው ሚካኤል ጽጌ ድብደባና ዝርፊያ በዲሲ (20)

በአለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተ የኢንተርኔት መሰረተ-ልማት መቋረጥን ተከትሎ በርካታ ድርጅቶችና አገልግሎት ሰጪዎች ስራቸውን እንዲያቆሙ ተገደዋል። የዲሲ ሜትሮን ጨምሮ በርካት የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አገልግሎት ተቋርጧል ወይንም ተስተጓግሎ ነበር። የዲሲ ሜትሮ በትዊተር ገጹ አገልግሎት እንደሚዘገይ ያስታወቀ ሲሆን ከሰዓታት በኋላም አገልግሎት ሳይስተጓጎል እንደጀመሩ አስታውቀዋል።

በተጨማሪም በአንዳንድ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የድንገተኛ አደጋና የፖሊስ ስልክ 911 አገልግሎት መስጠት አቁሞ ነበር።

ልክ እንደትራንስፖርቱ ዘርፍ በርካታ የሚዲያና ብሮድካስት አገልግሎት ሰጪዎች ፕሮግራሞቻቸውን ማስተላለፍ ባለመቻላቸው ተቋርጠው እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል። ባንኮችም እንዲሁ የሲስተም መቋረጥ ደርሶባቸዋል።
የዚህን መቆራረጥ ያስከተለው በማይክሮሶፍት ክላውድ ላይ በ3ኛ ወገን የተደረገ ማሻሻያ (አፕዴት) ተከትሎ እንደእሆነ ማይክሮሶፍት አስታውቋል።


ይህን ተከትሎም በርካታ የመንግስት አካላት የድንገተኛና አስቸኳይ ጊዜ አሰራር ተግባራዊ አድርገዋል። በሜሪላንድ ስቴት የድንገተኛ አስቸኳይ ጊዜ ፕላን ከኖርማል ወደ ከፊል ድንገተኛ ከፍ ብሏል ሲል ቢሮው በትዊተር ገጹ አስታውቋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.