የሊሞ ሹፌር የሆነው ሚካኤል ጽጌ ድብደባና ዝርፊያ በዲሲ (19)

ዛሬ ቅዳሜ በበትለር ፔንሳልቫንያ የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን እያደረገኡ በነበረበት ወቅት የቀድሞው ፕሬዘደንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው በርካታ ምንጮች አሳውቀዋል።


በተደረገባቸው ተኩስም ዶናልድ ትራምፕ ጆሯቸው እየደማ እንደነበር ታውቋል። የግድያ ሙከራው በተደረገበትም ቅጽበት የሴክሬት ሰርቪስ ጥበቃዎቻቸው ከአካባቢው በፍጥነት አሽሽተዋቸዋል።


የአካባቢው አቃቤህግም ተኳሹና አንድ ሌላ የፕሮግራም ተሳታፊ ለህልፈት ተዳርገዋል። ሴክሬት ሰርቪስ ሁለት ተጨማሪ ታዳሚዎች ለከፋ ጉዳት እንደተዳረጉ አሳውቋል::


በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ ዶናልድ ትራምፕ በተኩሱ የቀኝ ጆሯቸውን የላይኛውን ክፍል እንዳቆሰለው ተናግረዋል
ተኳሹን የሴክሬት ሰርቪስ ፖሊሶች እንደገደሉት ታውቋል።

ቢቢሲ ያናገረው አንድ የአይን እማኝም ስናይፐር ይዞ ጣራ ላይ ሰው እንዳየና ለፖሊስና ለሴክሬት ሰርቪስ ፖሊሶች እንደነገራቸው ነገር ግን ምንም እንዳላደረጉ በኋላም ይህ ሰው የቀድሞው ፕሬዘደንት ላይ እንደተኮሰባቸው ተናግሯል።

የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘርም ዜናውን እንደሰሙና ለትራምፕም፤ በሁኔታው ለተጎዱት ሌሎችም እንዲሁም ለአገሪቱ እንደሚጸልዩና በበለጠም ከከተማዋ የፖሊስ አለቃ ስሚዝ መረጃ እንደደረሳቸውና ከፌደራል ፖሊስ አባላትጋ በቅርብ ሆነው የከተማቸውን ሰላም ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ በትዊተራቸው ለጥፈዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.