12/12/2024
Add a heading (1)

የዩናይትድ ስቴትስ አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ ሊከናወን ሁለት ወር ብቻ ቀርቶታል። ይህን ተከትሎም በየአካባቢው ያሉ የምርጫ ተወዳዳሪዎች የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን አጠናክረዋል። በዘንድሮው ምርጫ ለፕሬዘደንትነት የሚወዳደሩትን የቀድሞ ፕሬዘደንት ዶናልድ ትራምፕና የአሁኗ ምክትል ፕሬዘደንት ካማላ ሀሪስ ፉክክር በዋናነት ይጠበቃል። በመቀጠልም በየስቴቱ ያሉትን የሴኔት መቀመጫዎች ለመቆጣጠር ያለው ፉክክር በተለይም ሁለቱ ፓርቲዎች በሴኔት ያላቸውን የበላይነት ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል።

እስከባለፈው ሳምንት በተሰሩ የቅድመ ምርጫ ምዘናዎች (Poll) ለሜሪላንድ የሴኔት መቀመጫ የሚወዳደሩት የዴሞክራት እጩዋ አንጀላ ኦልሶብሩክና የሪፐብሊካን እጩው ሌሪ ሆጋን በአቻ 46% ላይ ይገኙ የነበረ ሲሆን ዛሬ ሴፕቴምበር 4 በወጣ ሪፖርት አንጀላ ኦልሶብሩክ በ46% ባሉበት ሲቀጥሉ ሌሪ ሆገን ደሞ በ5 ነጥብ በመንሸራተት በ41 ፐርሰንት ይከተላሉ ሲል የጎንዛሌዝ ሪሰርችና ሚድያ ተቋም አስታውቋል። ኢትዮጲክ በበኩሏ በአንባቢዎቿ ላይ በተደረገና 160 ሰዎች በተሳተፉበት ተመሳሳይ ምዘና 72% አንባቢዎቻችን ሌሪ ሆገንን እንደሚመርጡ ያሳወቁ ሲሆን 18% አንጀላ ኦልሶብሩክን እንደሚመርጡ ጠቁመዋል። 6% የሚሆኑት እስካሁን ማንን እንደሚመርጡ ያልወሰኑ ሲሆን 4% ደሞ ማንንም እንደማይመርጡ አሳውቀዋል።

እኛም ይህን በማስመልከት ባሳለፍነው ሳምንት ቃል በገባነው መሰረት የእናንተ የአንባቢዎቻችንን ጥያቄዎች ይዘን ለሜሪላንድ የሴኔት መቀመጫ እየተወዳደሩ የሚገኙትን የቀድሞውን የሜሪላንድ ገቨርነር ላሪ ሆጋንን ለጥያቄ ጋብዘናቸው ምላሻቸው ቀና ሆኖ በፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ በሚገኘው የፔይንት ብራንች ኤለመንተሪ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች የተለያዩ የመማሪያ ቁሶችን በሚለግሱበት ወቅት እዛው ተገናኝተን ለተወሰኑ ጥያቄዎቻችን ምላሽ ሰተውናል በሜሪላንድ ለሚኖረው የኢትዮጵያዊና ብሎም አፍሪካዊ ማህበረሰብም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የጊዜ ጉዳይ ሆኖ አንባቢዎች የላኩልንን ጥያቄዎች በሙሉ መጠየቅ ባንችልም፤ ከምርጫው በፊት ለሌላ ቃለመጠይቅ ፍቃደኛ በመሆናቸው እዚህ ላይ ያልጠየቅናቸውን ጥያቄዎቻችሁን ይዘን ሄደን መልስ ይዘን ለመምጣት እንሞክራለን። ለዛሬ ግን የሌሪ ሆጋንን ቆይታ ከኢትዮጲክጋ እነሆ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት