12/12/2024
Add a heading

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ህገ ወጥ የጦጣ ንግድ ላይ ለተሰማሩ የካምቦዲያ ነጋዴዎች ጦጣዎችን የማጏጏዝ ስራ የተቃወሙ የእንስሳት ደህንነት ተንከባካቢዎች ከሰሞኑ በደለስ አየርማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመገኘት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል::

በተለምዶ ፒታ የሚባለው የፒፕል ፎር ዘ ኤቲካል ትሪትመንት ኦፍ አኒማልስ የተባለ የእንሣት ደህንነት ተንከባካቢ ተቋም ላለፉት ጥቂት ወራት ሲያደርገውን የነበረውን ተቃውሞ በማጠናከር ከሰሞኑ በደለስ አየር ማረፊያ በሳጥን ውስጥ በተገጠመ ስፒከር የሚሰቃዩ የጦጣ ድምጽ በማሰማት በቦታው ለነበሩ ተጓዦች የግንዛቤ ማስጨበጫ ተቃዎሞ እንዳደረጉና የአየር መንገዱ እንዲህ ካለው የጭካኔ ተግባሩ እንዲታቀብ ጠይቀዋል።


ተቋሙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ህገወጥ ለሆኑ የጦጣ ነጋዴዎች የበረራ አግልግሎት ከመስጠቱም በላይ በቅርቡ ከ250 በላይ ባለረጅም ጭራ ማኪስ የተባሉ ሊጠፉ የተቃረቡ የጦጣ ዝርያዎችን በዘግናኝ መንገድ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ማጓጓዙን በመግለጫቸው አሳውቀዋል።

በተጨማሪም አየርመንገዱ በደቡባዊ ማስራቅ ከሚገኝና በህገወጥ የጦጣ ንግድ ከተሰማራ የጥቁር ገበያ ቡድን ጋ እንደሚሰራ በመግለጫው ተጠቅሷል።

እነዚህን ጦጣዎች ለምርምርና ለላቦራቶሪ መሞከሪያነት የሚገለገሉ ተቋማት በሜሪላንድ ፍሬደሪክ የሚገኘው የቻርልስ ሪቨር ላቦራቶሬስ እና የፕሪላብ እንደሆኑም ተጠቅሷል።

አየር መንገዱ በጁላይ 16 2023 ላይ 336 ጦጣዎችንከሞሪሸስ አትላንታ ሲያጓጉዝ ስለጦጣዎቹ አመጋገብና ውኃ ፕሮግራም የሚያመላክት መረጃ በግልጽ ቦታ ባለመገኘቱ ማስጠንቀቂያ ወቶበት ነበር።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት