በአሰቲግ ደሴትና ደቡባዊ ኦሽን ሲቲ የህክምናና ከህክምና ጋ የተያያዙ ቆሻሻዎች በውሃ ተንሳፈው መምጣታቸውን ተክትሎ የኦሽን ሲቲ ቢችና የአሰቲግ ደሴት ፓርክ ለህዝብ ዝግ ሆነዋል።
ባለስልጣናት ዛሬ እሁድ ሴፕቴምበር 15 ከሰዓት እንዳሳወቁት መዝናኛ ቦታዎቹ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ያሳወቁ ሲሆን ምን አይነት ቆሻሻ እንደተገኘ ግን ይፋ ከማድረግ ተቆጥበዋል።
በጉዳዩ መልዕክት ያስተላለፉት የድንገተኛ ጉዳዮች አገልግሎት ዳይሬክተር ጆ ቲዮባልድ እንዳሉት በጉዳዩ ላይ እርግጠኞች እስከሚኮን ድረስም ወደቢች ሰዎች ባይሄዱ እንደሚመረጥ ተናግረዋል። ወደ ቢቹ እንሄዳለን የሚሉ ሰዎች ደሞ ጫማ አርገው እንዲሄዱ መክረዋል።
አክለውም የኦሽን ሲቲ ባለስልጣናት ከዎርቼስተር ካውንቲ ባለስልጣናትጋ በመሆን የዚህን ቆሻሻ መነሻ ለማወቅ የማጣራት ስራ መጀመራቸውን አሳውቀዋል።
የአሰቲግ ደሴት ደቡባዊ ክፍል ከቨርጂንያጋ የሚዋሰ ቢሆንም ቆሻሻው የተገኘው በሜሪላንድ በኩል ብቻ እንደሆነ ተነግሯል።