ዋሽንግተን አሶሼትድ ፕሬስ ዛሬ እንደዘገበው ዛሬ ሴፕቴምበር 15 2024 ፍሎሪዳ በሚገኙት በዶናልድ ትራምፕ አቅራቢያ የጥይት ተኩስ እንደነበረ የሴክሬት ሰርቪስና የፕሬዘደንቱ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ያሳወቀ ሲሆን ፕሬዘደንቱ ላይ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰ አክለው አሳውቀዋል።
በሪፖርቱ የጥይት ተኩኡ የቀድሞውን ፕሬዘደንት ላይ ያነጣጠረ ይሁን አይሁን አልተገለጸም።
በጉዳዩ ላይ ለፕሬዘደንት ጆ ባይደንና ለካማላ ሀሪስ መረጃው እንደደረሳቸውና ምርመራውን በአንክሮ እየተከታተሉት እንደሆነ ከዋይት ኃውስ ተጠቁሟል። የቀድሞው ፕሬዘደንት ትራምፕ ደህና በመሆናቸውም ረፍት እንደተሰማቸው ጨምረው ገልጸዋል።
ሴንተር ሊንድሴይ ግራሃም በበኩላቸው በትዊተር ገጻቸው ላይ ከተኩሱ በኋላ ከትራምፕጋ በስልክ እንዳወሩና ዶናልድ ትራምፕ በጥሩ መንፈስ ላይ እንደሚገኙና ከሚያውቋቸው ጠንካራ ሰዎች አንዱ እንደሆኑም አሳውቀዋል።
አሶሼትድ ፕሬስ ከኤፍ.ቢ.አይ ሰማሁት ባለው መረጃ ዶናልድ ትራምፕ በፓልም ቢች አቅራቢያ ባለው ቤታቸው ጎልፍ ብምጫወት ላይ ሳሉ ሌላ የግድያ ሙከራ እንደተደረገባቸው ተጠቁሟል::
በአካባቢውም የክላሽ (AK-47) ጠብመንጃ ተገኝቷል:: ድርጊቱን ፈፅሟል የተባለውም ሰው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል::
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን። ዜናው የአሶሼትድ ፕሬስ ነው።