Customize Consent Preferences

We use cookies to help you navigate efficiently and perform certain functions. You will find detailed information about all cookies under each consent category below.

The cookies that are categorized as "Necessary" are stored on your browser as they are essential for enabling the basic functionalities of the site. ... 

Always Active

Necessary cookies are required to enable the basic features of this site, such as providing secure log-in or adjusting your consent preferences. These cookies do not store any personally identifiable data.

No cookies to display.

Functional cookies help perform certain functionalities like sharing the content of the website on social media platforms, collecting feedback, and other third-party features.

No cookies to display.

Analytical cookies are used to understand how visitors interact with the website. These cookies help provide information on metrics such as the number of visitors, bounce rate, traffic source, etc.

No cookies to display.

Performance cookies are used to understand and analyze the key performance indexes of the website which helps in delivering a better user experience for the visitors.

No cookies to display.

Advertisement cookies are used to provide visitors with customized advertisements based on the pages you visited previously and to analyze the effectiveness of the ad campaigns.

No cookies to display.

Screenshot

Screenshot

ድምፃዊት አስቴር አወቀ፣ አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ እና ሌሎች ሶስት ሴት ኢትዮጵያዊያኖች በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ሊሸለሙ ነው።

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የተመሰረተውና ለትርፍ ያልተቋቋመው ኖቫ ኮኔክሽን የሚያዘጋጀው የ2024 አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ የዘንድሮ የክብር ተሸላሚዎች ታውቀዋል። ይህ አመታዊ የእውቅና ሽልማት ስነ ስርአት በአሜሪካና በአፍሪካ በሙያቸው ታላቅ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን ለማክበር የተዘጋጀ ነው። በየአመቱ ከስፖርት፣ ከስነ ጥበብና ከስራ ፈጠራ ዘርፎች ለማህበረሰቦቻቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦና ለለውጥ ላደረጉት የላቀ ተሳትፎ ከየዘርፉ ተመርጠው የሚሸለሙበት መድረክ ነው።

አፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ እስካሁን ለአራት ጊዜያት ተካሂዷል። እውቅና ከተሰጣቸው ተፅዕኖ ፈጣሪዎች መካከል ደግሞ የሚከተሉት ይገኙበታል፦

2019: ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን( ቴዲ አፍሮ)፣ አትሌት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና ሚስተር ማርክ ጌልፋንድ

2020: በኮቪድ-19 ምክንያት አልተካሄደም

2021: አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ፣ ድምፃዊ ኤኮንና አቶ በረከት ወልዱ

2022: አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ “እረኛዬ” የቴሌቪዥን ድራማ፣ አቶ ሄኖክ ተስፋዬ እና ንግስት ሰናይ ልኬ

2023: የዲባባ ቤተሰብ፣ አቶ ግርማ ዋቄ፣ አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄና አትሌት ስለሺ ስህን

ዘንድሮም በተለያዩ ዘርፎች አምስት ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያዊያንን ለማክበርና እውቅና ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል፤ የዚህ አመት ተሸላሚዎች በሙሉ ሴቶች ናቸው። በስነ ጥበብ ዘርፍ ዝነኛዋ ድምፃዊት አስቴር አወቀና አንጋፋዋ ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ፣ በስፖርቱ ዘርፍ የማራቶንና የ5000 ሜትር የአለማችን ክብረወሰን ባለቤቶች ትዕግስት አሰፋና ጉዳፍ ፀጋዬ እንዲሁም በቢዝነስ ዘርፍ ርብቃ ሀይሌ ተሸላሚዎች ይሆናሉ።

በእለቱ የዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ሴናተሮች፣ ከንቲባዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረጋላቸው በርካታ እንግዶች ይገኛሉ፤ ተሸላሚዎቹ ከግዛቶቹና ከተማዎቹ ተወካዮች የእውቅና ሰርተፍኬት ይበረከትላቸዋል።

በተጨማሪ ለበጎ አድራጎት ስራ የሚውል የሙዚቃ ዝግጅት በወጣቷ ድምፃዊት ራሄል ጌቱና በታዋቂው መሳሪያ ተጫዋች ሰላም ስዩም የሚቀርብ ይሆናል።

የ2024 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ ስነ ስርአት ሜሪላንድ በሚገኘውና ኢትዮጵያዊያን በባለቤትነት በሚያስተዳድሩት ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል እሁድ ኦክቶበር 13/2024 ምሽት በደማቅ ዝግጅት ይካሄዳል።

ኖቫ ኮኔክሽን

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.