በሜሪላንድን የዴሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው በዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት ለመመረጥ እየተፎካከሩ ያሉት የአሁኗ የፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ ኤክስኪውቲቭ የሆኑት አንጀላ ኦልሶብሩክ በሜሪላንድና በዲሲ በስማቸው ተመዝግበው ከሚገኙ የመኖሪያ ቤቶቻቸው ያልተገባ የታክስ ቅነሳ ተጠቃሚ ሆነዋል ሲል ሲኤንኤን ትላንት ዕሁድ ሴፕቴምበር 22 2024 ባወጣው ዘገባው አስታውቋል፡፡
እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ከሆነ በዲሲ ኖርዝ ኢስት በሚገኘውና በስማቸው በተመዘገበው ቤት ምንም እንኳ እድሜያቸው ለአዛውንት ጥቅማጥቅሞች ያልደረ ቢሆንምና በህጉ ይህ ባይገባቸውም የአዛውንቶች የታክስ ቅነሳን በመጠቀም በሺዎች የሚቆጠር ዶላር ማትረፋቸውን ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም በሁለቱም ቤቶች ላይ በቋሚ የመኖሪያነት የሚገኙ ጥቅሞችን ከ10 ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ ወስደዋል፡፡ የኤክስኪውቲቯ አማካሪ ለሲኤን ኤን እንዳስረዱት ካውንቲ ኤክስኪውቲቭ አንጀላ ኦልሶብሩክ ስለዚህ ግድፈት እንዳላወቁና ጠበቃቸው በዲሲም በፕሪንስ ጆርጅም ያሉትን ቤቶች የተፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከል እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አንጀላ ኦልሶብሩክ የመጀመሪያዋ ሴት የስቴት አቶርኒ ሆነው የተመረጡ እና የመጀመሪያዋ የሴት የካውንቲ ኤክስኪውቲቭ በመሆን የተመረጡ ታሪክ ሰሪ ናቸው፡፡
ሙሉ ዝርዝሩን ለማየት የሲኤን ኤን ን ዘገባ ሊንኩን በመጫን ያገኛሉ፡፡