በኦገስት ተመርቀው የተጀመሩትና እስካሁን ማስጠንቀቂያ ብቻ ሲሰጡ የነበሩት የፍጥነት መቆጣጠሪያ ካሜራዎች ስራ ጀምረዋል፡፡ የቅጣት ትኬትም መላክ ተጀምሯል፡፡
የአርሊንግተን ካውንቲ ፖሊስ የ2024/25 የትምህርት ዘመን መጀመርን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ለመጪው የትምህርት ዘመን አስር አዳዲስ የፍጥነት መቆጣጠሪያ የትራፊክ ካሜራዎችን በህዝብ ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ መትከሉንና ይህም በትምህርት ተቋማት አካባቢ የተሽከርካሪ አላግባብ ፍጥነት የሚያስከትለውን ጉዳት መቀነስ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
IMAGE: From Arlington County Police Facebook page.
እነዚህ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ካሜራዎች ከኦገስት 26 እስከ ሴፕቴምበር 24 በፍጥነት ሲያሽከረክሩ ለያዟቸው አሽከርካሪዎች ማስጠንቀቂያ በመላክ ስራ የጀምውሩ ሲሆን ከትላንት መስከረም 25 ጀምሮ ደሞ የ100$ የትራፊክ ቅጣት ቲኬት መላክ እንደጀመሩ ተነግሯል፡፡
እነዚህ የፍጥነት መቆጣጠሪያ ካሜራዎችም በሚከተሉት ቦታዎች ላይ እንደተገጠሙ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
NB 1300 block of Kirkwood Road
WB 5800 block of Wilson Boulevard
SB 400 block of N. George Mason Drive
SB 600 block of S. Carlin Springs Road
SB Unit block of S. Carlin Springs Road
SB 1900 block of S. George Mason Drive
NB 1900 block of S George Mason Drive
SB 1200 block of S. George Mason Drive
EB 4500 block of Washington Boulevard
EB 5200 block of Yorktown Boulevard