12/12/2024
Cheesebur Day (9)

ወደምድር ሲደርስ ከኸሪኬን ወደ ስቶርም የተቀየረው የኸሪኬን ሄሊን በቨርጂንያ በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት እንዳደረሰ የቨርጂንያ ገዢ ገቨርነር ያንግኪን ተናገሩ። እንደ ገቨርነር ያንግኪን የህልፈት አደጋው የደረሰው በወደቀ ዛፍ ምክንያት ነው።
እንደ ያንግኪን ገለጻ ይህ ስቶርም ገና አልፎ እንዳላለቀና ተጨማሪ ዝናብና ውሽንፍር እንደሚመጣ ተናግረዋል። ነዋሪዎችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ በቀጥታ ገብተው ተናግረዋል።

ቨርጂንያ ቢችን ጨምሮ የቨርጂንያ ማዕከላዊ፤ ደቡባዊና ምስራቃዊ አካባቢዎች የቶርኔዶ ማስተንቀቂያ እንደወጣባቸውና በዳንፊልድ በስተሰሜን ቶርኔዶ ተከስቶ እንደነበር አብራርተዋል።

ገቨርነር ያንግኪን አክለውም በደቡባዊ ቨርጂንያ ላይ በጣለው ዝናብ ምክንያት ደራሽ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ የድንገተኛ አደጋ ተከላካይ ሰራተኞች 50 ሰዎችን ከጎርፍ አደጋ ታድገዋል በለዋል።


በዚሁ አካባቢም ከ240 ሺ በላይ ደንበኞች መብራት እንደጠፋባቸው ያሳወቁ ሲሆን ነዋሪዎች እጅግ እንዲጠነቀቁና ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ መክረዋል። የጠፋውን መብራት ለመጠገን ጊዜ ሊወስድ እንደሚችልም አብራርተዋል።


ሙሉ ቪዲዮውን ይህን ተጭነው ማየት ይችላሉ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት