በቀጣይ 1 አመት ለሚሆን ጊዜ የኢትዮጲክ መረጃዎች በዚህ መጠይቅ ላይ ተመስርተው የሚዘጋጁ በመሆኑ እባክዎን እንዳያመልጥዎ።
ኢትዮጲክ ለ3 ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በዋናነት በድረ-ገጿ www.ethiopique.com ና በፌስቡክ https://www.facebook.com/ethiopique202 በዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ የሚገኘውን አማርኛ አንባቢ ማህበረሰብ ከወሳኝ መረጃዎችጋ የማገናኘት ስራ ስትሰራ ነበር። ይህን አገልግሎት በቀጣይ በይዘትና በጥራት የተሻለ እንዲሆንና በተለይም አንባቢዎቻንን በብዛት ባሉበት አካባቢዎች ያሉ መረጃዎችንና መልካም አጋጣሚዎችን በሚገባ አጣርቶ ለማምጣት ይህን መጠይቅ አዘጋጅተናል።
የምናመጣቸው መረጃዎች እናንተን በደንብ እንዲጠቅሙና የናንተን ፍላጎት ለመረዳት የኢትዮጲክ ባልደረቦች ይህን መጠይቅ አዘጋጅተዋል። እናንተም የበለጠ ማወቅ የምትፈልጉት መረጃ በተለይም በመኖሪያችሁ አካባቢ ያሉ ጉዳዮች ላይ የምትፈልጉ ከሆነ፤ ብዙ ጊዜ እኛ የረሳናቸው ጉዳዮች ካሉ፤ ወይንም እናንተ አውቃችኋቸው ሌሎችም ቢያውቋቸው ይጠቀማሉ የምትሏቸው ጉዳዮች ካሉ በዚህ መጠይቅ ግቡና አጋሩን።