12/12/2024
img_7945-1

ኦክቶበር 1 – በወደብ ሰራተኞች የህብረት ስራ ማህበር የተጠራው የስራ ማቆም አድማ ተጀምሯል:: የቦልቲሞር ወደብ አስተዳደርም ይህን ደብዳቤ አውጥቷል::
ሁለቱም ወገን ተቀራርበው እንዲወያዩም መክሯል::
ሰራተኞች ከወደብ ውጭ የሚያከናውኑትን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅም ከህብረት ስራ ማህበሩጋ በቅርበት እንደሚሰራ አስረድቷል::

——-

ሴፕቴምበር30- ቦልቲሞርን ጨምሮ ከቴክሳስ እስከ ሜይን በተዘረጋው የአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የተመሰረቱት ወደቦች ላይ የሚሰሩ 45 ሺህ ሰራተኞች የክፍያ ማሻሻያ ካልተደረገላቸው ከዛሬ ለሊት ጀምሮ ስራ እንደሚያቆሙ በህብረት ስራ ማህበራቸው አማካይነት አስፈራርተዋል፡፡ ይህም የአገሪቱን ኢኮኖሚ በቀን 5ቢልየን ዶላር እንዲከስር ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የፕሬዘደንት ባይደን አስተዳደር ሰራተኞችና ባለሐብቶች ልዩነታቸውን በድርድር እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡
ይህ የስራ ማቆም አድማ ከተደረገና ለቀናት ከቀጠለ ከፍተኛ የኑሮ ውድነትና ቀውስ ያስከትላል ተብሏል፡፡ ምግብና መጠጥን ጨምሮ ሌሎች ለህይወት አስፈላጊ የሆኑ ቁሶች እጥረት ሊከሰት እንደሚችልም ተተንብዩአል፡፡
ዎልማርትና ኮስኮ የሸማቾችን ፍላጎት ለማሟለት የተቻላቻቸውን እየሰሩ እንደሆነ የሬውተርስ ዘገባ ጠቁሟል፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት