የዋሺንግተን ዲሲ የአነስተኛ እና የአካባቢ ንግድ ልማት ዲፓርትመንት (DSLBD) ለመጀመሪያው ዙር የምግብ ተረፈ-ምርት ፈጠራ ስራዎች/ኃሳቦች ባለቤር ከሆኑ አነስተኛ ድርጅቶች ማመልከቻዎችን ይቀበላል።
ይህ ድጋፍ ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩና በዋናነት የምግብ ተረፈ-ምርትን ለመቀነስ አላማው በማድረግ ለምግብ ቤቶች፣ ለምግብ አምራቾች፣ ለጋራ የንግድ ኩሽናዎች፣
እና እንደ ዋና ጎዳናዎች እና የንግድ ማሻሻያ ወረዳዎች ያሉ የንግድ ኮሪደሮች በውድድር ያሳትፋል።
በዲስትሪክቱ የምግብ ንግዶች ውስጥ የምግብ ተረፈ-ምርትን መቀነስ የምግብ እና የቆሻሻ ወጪዎችን ይቀንሳል፤ አይጦችን ይቀንሳል እናም የካርበን ልቀትን ይቀንሳል.
ለውድድሩ የማመልከቻ የመጨረሻ ቀን በጃንዋሪ 31፣ 2022 ከሰዓት 2 ሰዓት (2:00 PM) ነው።
አመልካቾች በአንድ የውድድር ማመልከቻ ሶስት ጥቅሞችን ማግኘት ይችላሉ፡-
ቨርቿል ወይም በአካል የምግብ ቆሻሻ ግምገማ፡ እነዚህ ነጻ እና ለሁሉም ብቁ አመልካቾች የሚሰጡ ይሆናሉ፣ በዚህ ፕሮግራም የሚካተቱ ድርጅቶች የምግብ ብክነትን እንዴት መቀነስ እንደሚቻል ምክሮች ይሰጣል።
ኮምፖስት ክሬዲት፡ 100 የንግድ ድርጅቶች እያንዳንዳቸው የ$1,000 ዶላር ክሬዲት የሚያገኙ ሲሆን የምግብ ተረፈ-ምርቶቻቸውን ተሰብስቦ ለማዳበሪያነት እንዲያገለግል ይደረጋል።
የምግብ ተረፈ-ምርት የፈጠራ ኃሳብ ድጋፎች፡ DSLBD በ2022 የበጀት ዓመት ከ6 እስከ 20 የሚደርሱ የኃሳብ አፍላቂዎችን አወዳድሮ በድምሩ 300,000 ዶላር ይሰጣል።
ለበለጠ መረጃ ይህን ይጫኑ
ለማመልከት ስለሚያስፈልጉ ዶክመንቶች ይህን ይጫኑ
በውድድሩ ለመካፈል ይህን ይጫኑ
ለማመልከት ሁሉም አስፈላጊ መረጃዎች በFood Waste Innovation Grant RFA ውስጥ ይገኛሉ።