
አርብ ጃንዋሪ 17-2025- የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ቲክቶክ ለአሜሪካ ባለሀብቶች ካልተሸጠ በጃንዋሪ 19 እንዲዘጋ በስር ፍርድ ቤቶች የተወሰነውን ውሳኔ ያለተቃውሞ በሙሉ ድምጽ ደግፎታል።
ፍርድ ቤቱ እንዳለው ቲክቶክ ከ170 ሚልየን ተጠቃሚዎቹ የመናገር ነጻነት አንጻር ከቻይና መንግስትጋ ያለው ቁርኝት ለአገር ደህንነት አስጊ እንደሆነና ይህን ተከትሎም የግድ ለአሜሪካ ባለሀብቶች ተሸጦ በአሜሪካ ህግ እንዲዋቀር ሀሳቡን ሰቷል።
ቲክቶክ ከጃንዋሪ 19 ጀምሮ ከአፕስቶርና ከፕሌይ ስቶር ሲወርድ ሰዎች መተግበሪያውን መጫን እንደማይችሉ ሆኖም አስቀድመው የጫኑ ሰዎች ግን መጠቀም እንደሚችሉ አስረድተው ሆኖም አዳዲስ አፕዴቶችን መጫን ስለማይችሉ በጊዜ ሂደት አገልግሎቱ እንደሚቋረጥ አስታውቀዋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ መጪው ፕሬዘደንት ትራምፕ ከቲክቶክጋ የተሻለ መግባባትን በመፍጠር መተግበሪያ በአሜሪካ እንዳይቋረጥ እንደሚያደርጉ በተለያየ ጊዜ ያሳወቁ ሲሆን በምን አይነት መንገድ ይህን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ እስካሁን አይታወቅም።