Screenshot 2025-01-16 at 8.37.16 PM

ምስል፤ ከጎፈንድ ሚ ገጻቸው

ከሰሞኑ በፌርፋክስ ፖሊስ አፋልጉኝ ጥሪ ቀርቦበት የነበረውና በኋላም በፖሊስ ህልፈቱ የተነገረው የታምራት ገብረሚካኤል ቤተሰቦች ለቀብርና ለሌሎች ወጪዎች የሚሆን ድጋፍ ጠይቀዋል። ለዚህ ድጋፍ ከተዘጋጀው የጎ ፈንድ ሚ ገጽ ላይ እንዳገኘነው መረጃ ከሆነ ታምራት ጠፍቶ ከነበረበት ከጃንዋሪ 5፣ 2025 ጀምሮ፣ ቤተሰብ ወዳጆችና ማህብረ ሰቡ ሁሉ እርሱን ለመፈለግ ያላሰለሰ ጥረት ቢያደርጉም፣ በጃንዋሪ 14፣ 2025 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የታምራት ህልፈተ ህይወት ሚስቱን ፌቨንና የ9 እና የ11 ዓመት ልጆቹን አንዲሁም ቤተሰቡን በጥልቅ ሃዘን ላይ ጥሏል።

ቤተሰቦቹ አክለውም “በዚህ ድንገተኛ ክስተት፣ ታታሪ፣ አፍቃሪና ደግ አባት ያጣው ቤተሰብ በከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ይገኛል። እስካሁን አብራችሁ በጸሎትና በድጋፍ የቆማችሁትን ሁሉ በማመስገን፣ ለታምራት ቀብር እንዲሁም ለቤተሰቡ መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን ልግስናችሁን ለመጠይቀ በፊታችሁ በትህትና ቀርበናል። ለዚህም የሚሆን የጎ-ፈንድ ሚ ፔጅ አዘጋጅተናል።” ያሉ ሲሆን ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ለማግኘት ካቀዱት የ30ሺ ዶላር መዋጮ 18,975 ብቻ እንደሰበሰቡ ታውቋል።

ምስል፤ ከጎፈንድሚ ገጽ

እርስዎም ይህን ቤተሰብ ለማገዝ ፈለጉ ይህን ሊንክ ተከትለው ወይም ከስር ያለውን ተጭነው ያቅምዎትን መለገስ ይችላሉ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.