Screenshot 2025-01-16 at 8.15.18 PM

ምስል፡ ከዲሲ እሳትና ድንገተኛ አደጋ

አርብ ንጋት ላይ በወጣ ተጨማሪ መረጃ መሰረት ወንዝ ውስጥ የገባው መኪና አሽከርካሪ በአደጋው ለህልፈት እንደተዳረገ ተገልጿል። ከመጀመሪያው ሰው ሌላ ሁለተኛ ሰው ሬሳም ከወንዝ ውስጥ ወቷል። ተዘግተው የነበሩት መንገዶችም ክፍት ሆነዋል።

አርሊንግተን ሜሞሪያል ድልድይ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ መኪና ፖቶማክ ወንዝ ውስጥ እንደገባና ድልድዩ ረዘም ላለ ጊዜ ተዘግቶ እንደሚቆይ የዩ ኤስ ፓርክ ፖሊስ አስታወቀ።

ዛሬ ምሽቱን 6፡50 ገደማ ላይ በሁለት መኪኖች ላይ በደረሰ ግጭት አንደኛው መኪና ድልድዩን ዘሎ እንደገባና ሙሉ ለሙሉ እንደሰመጠ ፖሊስ ያስታወቀ ሲሆን ጠላቂ የነፍስ አዳኝ ሰራተኞች በቦታው ተገኝተው ነፍስ የማዳን ስራ እየሰሩ እንደሆነ ታውቋል። የዩ ኤስ ፓርክ ፖሊስ ይህንን ምርመራ በዋናነት እየመራው እንደሚገኝም የደብሊው ቲ ኦ ፒ መረጃ ያሳያል።

https://twitter.com/dcfireems/status/1880049302514593916

በአኩ ዌዘር ዩቲውብ ቻናል ላይ የተለጠፈው ቪዲዮ እንደሚያሳየው የድልድዮ መከለያ አጥር በአደጋው ሙሉ ለሙሉ ተደርምሷል።

ማምሻውንም የዩ ኤስ ፓርክ ፖሊስ ቃል አቀባይ ቶማስ ቱኔም በሁለት መኪኖች ግጭት አንድ መኪና ዘሎ ወንዝ ውስጥ የገባ ሲሆን አንዱ እዛው ድልድዩ ላይ ቀርቷል ሲሉ። ድልድዩ ላይ በቀረው መኪና ውስጥ የነበረ አንድ ሰው ቀላል ጉዳት ደርሶበት ወደሆስፒታል እንደሄደና ወደውሃ ከገባው መኪና ውስጥ ደሞ አንድ ሰው ሊወጣ እንደቻል ሆኖም ያ ሰው ለህይወቱ የሚያሰጋ ጉዳት እንደደረሰበትና ወደሆስፒታል እንደተወሰደ ገልጸዋል።

አደጋው አሁንም በምርመራ ላይ እንዳለ ጨምረው አሳውቀዋል። ሙሉ መግለጫውን ከኤቢሲ7 ከስር ማየት ይችላሉ።

ፎክስ 5 ዲሲ የተባለው የዜና ጣቢያ ከንግስቲ አዳነ አገኘሁት ብሎ ባጋራው ቪዲዮ እንደሚታየውም ነጭ ፒክ አፕ ትራክ ከፊቱ ያለ መኪናን በመግጨትና መኪናውን መቆጣጠር ባለመቻሉ ተጠምዝዞ ወደወንዙ ገብቷል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.