
በሜሪላንድ የታኮማ ፓርክ ፖሊስ ዛሬ ጃንዋሪ 16 ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ የ15 ዓመት ታዳጊ የሆነችው ህያብ አዘራ ወልደሀይማኖትን አፋልጉኝ ብሏል። ተፈላጊዋ ጃንዋሪ 13 2025 ንጋት 6:45am ላይ በ7700 Maple Avenue አቅራቢያ ለመጨረሻ ጊዜ እንደታየች ተነግሯል።
ታዳጊዋ ከሰኞ ጃንዋሪ 13 ጀምሮ በትምህርት ገበታዋ ላይ እንዳልተገኘችና ምናልባትም በአካባቢው ካሉ ከጓደኞቿ ጋ ልትሆን እንደምትችል ጠቁሟል። ህያብ ያለችበትን የምሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለፖሊስ በስልክ ቁጥር 301-270-1100 በመደወል ወይንም በቴክስት tip411 በማለት መጠቆም ይችላል።
