ቲክ

Update: -ሰበር ዜና- ቲክቶክ ተከፍቷል!! (እሁድ ጃንዋሪ 19 2025) 1:00pm

መጪው የአሜሪካ ፕሬዘደንት ዛሬ ዕሁድ ጃንዋሪ 19 በትሩዝ ሶሻል አካውንታቸው እንዳስታወቁት ቲክቶክ ተዘግቶ እንዳይቆይ ተቋማትን እንደጠየቁና ነገ ሰኞ ስራ ሲጀምሩ በኤግዚኩቲቭ ኦርደር እንዲዘጋ የተወሰነበትን የጃንዋሪ 19 ቀነገደብ በማራዘም ቲክቶክ እንዴት የደህንነት ስጋት ሳይሆን በአሜሪካ መስራት እንደሚችል እንደሚደራደሩ አስታውቀዋል።


ይህ ትዕዛዛቸውም እንደ አፕልና ጉግል ያሉ የቴክኖሎጂ ተቋማት ቲክቶክን ቢከፍቱ ቅጣት እንዳይጣልባቸው የሚያዝ ህግ አብረው እንደሚያጸድቁ ጠቁመዋል።ይህን ተከትሎም ቲክቶክ አፕ ከትላንትናው የተለየና አፑ የተዘጋው በጊዜያዊነት እንደሆነ የሚገልጽና በቅርቡ ተመልሶ እንደሚመጣ የሚናገር አዲስ ማስታወቂያ አውጥቷል።

ፕሬዘደንት ትራምፕ አሜሪካውያንና አለም አስደናቂውን የፕሬዘዳንታዊ በዓለ ሲመት ሊያዩት እንደሚገባ አብረው ተናግረዋል። ፕሬዘደንቱ ዩናይትድ ስቴትስ ቢያንስ 50 ከመቶ የቲክቶክን ድርሻ ባለቤትነት መያዝ እንዳለባትም አብረው ተናግራዋል።

ሙሉ የፕሬዘደንቱ ልጥፍ ከስር ያለው ነው።

I’m asking companies not to let TikTok stay dark! I will issue an executive order on Monday to extend the period of time before the law’s prohibitions take effect, so that we can make a deal to protect our national security. The order will also confirm that there will be no liability for any company that helped keep TikTok from going dark before my order.
 
Americans deserve to see our exciting Inauguration on Monday, as well as other events and conversations.
 
I would like the United States to have a 50% ownership position in a joint venture.  By doing this, we save TikTok, keep it in good hands and allow it to say up.  Without U.S. approval, there is no Tik Tok.  With our approval, it is worth hundreds of billions of dollars – maybe trillions. 
 
Therefore, my initial thought is a joint venture between the current owners and/or new owners whereby the U.S. gets a 50% ownership in a joint venture set up between the U.S. and whichever purchase we so choose.

ከሰሞኑ በርካቶች በቲክቶክ መዘጋት ማዘናቸውን የገለጹ ሲሆን ከደስታቸው ብዛትና የቲክቶክ ይዘጋ ጸሎታቸው በመሰማቱ ለእምነት ተቋማት ስዕለት ያስገቡ እንደነበሩም መረጃዎች ያሳያሉ።

የኢትዮጲክ ባልደረቦች በፌስቡክ ከወራት በፊት ባዘጋጁትና 371 አንባቢዎች በተሳተፉበት መጠይቅ መሰረት 75 ከመቶ የሚሆኑት አንባቢዎች መዘጋቱን ደግፈው ነበር።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.