
ዛሬ የዕውቁ የጥቁሮች መብት ተሟጋች የሆነውና በሰላማዊ ትግል ስትራቴጂው የሚታወቀው የዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ ቀን ነው።
እኛ ስደተኞች እዚህ መጥተን መብታችን ተከብሮልን፤ ሰርተን፤ ተምረን መለውጥ የምንችልበት መንገድ እንዲመቻችልን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የጥቁሮች የመብት ትግል (Civil Rights Movement) ዋነኛው ምክንያት ነው። እነሱ ታግለው የሰው መብት እንዲከበር በማድረጋቸው እንደኛ ያሉ ጥቁር ስደተኞች ተጠቃሚዎች የምንሆንበት የ1965ቱ የስደተኛና ዜግነት መብት(Immigration and Nationality Act of 1965) በህግ እንዲካተት በር ተከፍቷል። እንደ ኢትዮጲክ ከማንም በላይ ተሟግተው፤ ተገርፈው፤ በአደባባይ ተገድለው ተስፋ ሳይቆርጡ፤ ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለሌሎች መኖር ምን እንደሆነ አውርተው ሳይሆን ኖረው ያሳዩንን እንደነ ዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ያሉ በየዘመኑ ተሟግተው ያለፉና አሁንም እየታገሉ ያሉ የመብት ተሟጋቾችን እናመሰግናልን።
መልካም የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ ቀን ይሁንላችሁ!