ተገኝታለች (1)

ተፈላጊዋ ተገኝታለች። ሼር ያረጋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን

የባልቲሞር ካውንቲ ፖሊስ ትላንት ዕሁድ ጃንዋሪ 19 ባወጣው የአፋልጉኝ ጥሪ የ26 ዓመት ወጣት የሆነችውን መክሊት ያንተን ያያችሁ እባካችሁ ጠቁሙኝ ብሏል።

የፖሊስ መግለጫ እንደሚያሳየው መክሊት ቁመቷ 5 ጫማ ከ 2 ኢንች ሲሆን ክብረቷ ደሞ 121 ፓውንድ ነው ተብሏል። መክሊት ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው ዕሁድ ጃንዋሪ 19 2025 በግምት ጠዋት 9፡00am ገደማ በ ዊልኪንስ (Wilkens) አካባቢ ነው ተብሏል። መክሊት በወቅቱ የለበሰችው ልብስ ምን አይነት እንደሆነ እንደማይታወቅም መግለጫው ጠቁሟል።

ፖሊስ በመግለጫው መክሊት 4EZ1373 የሆነ የሜሪላንድ ታርጋ ያለው የ2017 ግራጫ ሱባሩ መኪና ይዛ ሳትሄድ እንዳልቀረ ጠቁሟል።

አክሎም መክሊት የስነ አዕምሮ ህመም/ጉዳት ሊኖርባት እንደሚችልና አቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋት ተነግሯል። ስለመክሊት መገኛ የሚያውቅ ወይንም ያለችበትን የሚያውቅ ለባልቲሞር ካውንቲ ፖሊስ በስልክ ቁጥር 410-887-0220 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

እናንተም ይህን መረጃ ሼር በማድረግ ተባበሯቸው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.