
በጎርጎሮሳውያኑ 2022 እና 2023 በዳውንታውን ሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ አካባቢ፤ በአካባቢው ባሉ የንግድ ሰዎች እና ነዋሪዎች ላይ ስጋት የፈጠረ ከፍተኛ ወንጀል ተዘግቦ የነበረ ቢሆንም፣ ይሁን እንጂ ከሰሞኑ ይፋ የተደረገ የባለፈው ዓመት የፖሊስ ሪፖርት በአካባቢው ወንጀል 7.6 ከመቶ መቀነሱን አመላክቷል።
የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሦስተኛው ክፍል ኮማንደር የሆኑት ጄሰን ኮኪኖስ ለጋዜጠኞች ጥረታቸው ስኬታማ እየሆነ መምጣቱን አስታውቀዋል።
ሆኖም ኮኪኖስ በመሃል ሲልቨር ስፕሪንግ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መቀነስ ቢያሳዩም፤ ነገር ግን አሁን ላይ የወጣት ታዳጊዎች ወንጀል በከባድ ችግር ነው መሆኑም በካውንቲው በተዘጋጀው መርሃግብር አክለው ተናግረዋል።
በተጨማሪም ኮማንደሩ ታዳጊ ወጣቶቹ መኪና መዝረፍን ጨምሮ፣ የመኪና ላይ የሚፈጸም ስርቆት ፣ እንዲሁም መኪና ይዘው የስርቆት ወንጀል መፈጸም ላይ በተለየ መልኩ ሲሳተፉ እያየን ነው ብለዋል።
ባለፈው ወር የተለቀቀው መረጃ እ.ኤ.አ. ከ2023 ከነበረው አንጻር 2024 ተመሳሳይ ወቅት ሲወዳደር ፣ የመኪና ስርቆት ከ 19 ወደ ስድስት በመውረዳቸው የወንጀል መጠኑ 68% መቀነሱን አመላክቷል።
በተመሳሳይ የዝርፊያ ወንጀል 24 ከመቶ ሲቀንስ፣ ግድያ ወንጀል ደግሞ በመቶ መቀነሱ ተመላክቷል።
በሞንትጎመሪ ም/ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑትና ሳምታዊ መግለጫውን ያዘጋጁት ኬት ስቱዋርት፤ ለወንጀል መቀነሱ በርካታ ምክንያቶችን የጠቀሱ ሲሆን፤ በመሀል ከተማ የመኪና ማቆሚያ ጋራጆች ውስጥ እና አካባቢ ያለው ደህንነት መጨመር፣ የፖሊስ አባላት ከመድረሳቸው በፊት ወንጀል በተፈጸመበት ስፍራ ቀድሞው ጥቅም ላይ የሚውሉ ድሮኖች ለተመዘገበው ለውጥ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የወጣት ታዳጊ ጥፋተኞች ማረሚያ ጉዳይ ውስብስብ እና ከባድ መሆኑንም ኮማንደሩ አስታውቀዋል።
የዲ.ሲ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር በቅርቡ በዋሺንግተን ዲሲ፤ ወጣት ታዳጊዎች ወንጀል ምርመራ ልዩ ክፍል እንደሚመሰርቱ የተናገሩ ሲሆን፤ ሁኔታው የዲሲ ተጎራባች ለሆነቸው ሜሪላንድ ግዛት ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ አዎንታዊ ውጤት እንደሚኖረውም ተገምቷል።