ዋሽንግተን ዲሲ፣ የዩናይትድ ስቴትስን ጦር ሠራዊት 250ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ለማክበር ጁን 14 ቀን 2025 አንድ ትልቅ ወታደራዊ የሰልፍ ትርዒት ታቅዷል። በዚህ ዝግጅት ላይ ከ6,000 በላይ ወታደሮች፣ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች፣ የጦር አውሮፕላኖች እንዲሁም በናሽናል ሞል ሙዚቃ፣ ርችት እና የመሳሪያ ትርኢቶች ያሉት የሙሉ ቀን በዓል ይኖራል። በተጨማሪም ይህ ቀን የባንዲራ ቀን እና የፕሬዝዳንት ትራምፕ 79ኛ የልደት ቀን ነው።
ጦር ሠራዊቱ ይህ ዝግጅት ረጅም ታሪኩን የሚያከብር እና ለመላው አሜሪካውያን የታሰበ እንደሆነ ይናገራል። ወታደሮች ታሪካዊ የደንብ ልብሶችን ይለብሳሉ እና ዘመናዊ መሣሪያዎች ለእይታ ይቀርባሉ። ለዓመታት ትልቅ የሰልፍ ትርዒት እንዲደረግ ሲገፋፉ የነበሩት ትራምፕ ይህ ትርዒት የዩናይትድ ስቴትስን ጥንካሬ እና ኩራት የሚያሳይ በመሆኑ ለፕሮግራሙ የሚወጣው የ45 ሚልየን ዶላር የገንዘብ ወጪ ይገባዋል ብለዋል።
የዚህ አላማ ደጋፊዎች ሰልፉ አርበኝነት የተሞላበት እና ወታደሮችን ለማክበርና ለማመስገን የሚረዳ ማሳያ እንደሆነ ያምናሉ። በተጨማሪም በ2026 የዩናይትድ ስቴትስን 250ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ለማክበር የታቀዱ ዝግጅቶችን ማስጀመሪያ በመሆን ያገለግላል ሲሉ ይደመጣሉ።
የዚህ ፕሮግራም ተቃዋሚዎች ደሞ ለአንድ ቀን ሰልፍ የሚወጣው 45 ሚልየን ዶላር እጅግ ውድ እንደሆነና ይህ በዕርግጥ አላማው የጦር ሰራውቱን ለማመስገ ወይስ ለፕሬዘደንቱ የግል ፍላጎት የሚለውን ጥያቄ ሲጠይቁ ይሰማሉ።
በተጨማሪም የዚህ ፕሮግራም ተቺዎች ታንኮች በመንገዶች ላይ ስለሚያደርሱት ጉዳት፣ በከተማ አገልግሎቶች ላይ ስለሚኖረው ጫና እና እንደ የምግብ ድጋፍና የቤት ኪራይ ድጋፍ የመሳሰሉ ወሳኝ ማህበራዊ ፕሮግራሞች በሚቆረጡበት በዚህ ጊዜ ለአንድ ቀን ፕሮግራም ይህን ያህል ገንዘብ ማባከን የሰዎችን ፍላጎት ያላገናዘበ ነው ይላሉ። ይህን ተከትሎም እንደ ስቲቭ ኮኸን ያሉ የዴሞክራት ፓርቲ ተወካዮች የአንድን ግለሰብ ልደት ወይም የስራ አፈጻጸም በተመለከተ የፌደራል መንግስቱ የጎዳና ትርዒቶች ላይ ገንዘብ እንዳያወጣ የሚከለከል ህግ አርቅቀው ለኮንግረስ አቅርበዋል።
የዲሲ ባለስልጣናት እስካሁን በይፋ በእቅድ ማውጣቱ ላይ አልተሳተፉም። ከንቲባዋ ሚውሪየል ባውዘር ከትራምፕጋ ላለመጣላት ነዋሪውንም ላለማስቀየም በጥንቃቄ ጉዳዩን የያዙት ሲሆን ለሰልፉ ፍቃድ ከመጠየቁ ውጪ ስለ ሰልፉ ዝርዝሩ እስካሁን አልታወቀም።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.