የሞንጎምሪ ካውንቲ ነዋሪዎች በኮቪድ ምክንያት ገቢያችሁ ከተቀዛቀዘ ከሰኞ ሜይ 16 ጀምሮ ለቤት ኪራይ እገዛ ማመልከት ትችላላችሁ። ይህ ፕሮግራም እንደ ዲሲው ስቴይ-ዲሲ ከሆነ ፈንዱ ሊያልቅ ስለሚችል አስቀድማችሁ ማመልከት ይመከራል። ስቴይ-ዲሲ ኦክቶበር 27 ላይ ሲዘጋ በጣም ብዙ ኢትዮጵያውያን ባለቀ ሰዓት ለማመልከት ሲሞክሩ ነበር ሆኖም ሳይጠቀሙበት አምልጧቸዋል።
ይህ ፕሮግራም ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። ለማመልከት ይህን ሊንክ ተጭነው። የማመልከቻውን ማስተማሪያ ቪዲዮ ለማየት ይህን ይጫኑ። ስለማመልከቻው በአማርኛ የተፃፈውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የኮቪድ ኪራይ ድጋፍ ፕሮግራም ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች ለማየት ይህን ይጫኑ፡፡