ናሎክሶን ወይንም ናርካን የተባለውና እንደ ሄሮይን፤ ፌንታኒል በመሳሰሉ አደንዛዥ እፅ ኦቨርዶዝድ የሆኑ ሰዎችን ከሞት የሚታደገው መድኃኒት በሁሉም የአርሊንግተን የህዝብ ቤተ-መፃህፍቶች ውስጥ ተካቷል።
ስለ ፌንታኒል ከኪንግ ካውንቲ ዋሽንግተን ድረ-ገፅ ያገኘነውን እነሆ
የFentanyl ማስጠንቀቂያ ለቤተሰቦችና ተማሪዎች
በሚያሳዝን ሁኔታ፥ በጊንግ ካዎንቲ ውስጥ በዋናነት ሕጋዊ ባልሆኑ የሚዋጡና ዱቄት ውስጥ በሚገኙ Fentanyl ምክንያት መድኃኒን ከመጠን በላይ በመውሰድ የሚከሰሞው ሞት ከቅርብ ጊዜ እየጨመረ ነው። ይህ ሞት ደግሞ በብዛት የሚከሰተው ዕድሜያቸው 18 ዓመትና ከዚያ በታች በሆኑት ላይ ነው።
ማስጠንቀቂያ:
ትክክለኛ ያልሆኑና ተመሳስለው የሚሰሩት ነገር ግን የታዘዙት የሚመስሉ ከሚዋጡ መድኃኒቶች ተጠንቀቁ። እነዚህ Fentanyl ሊኖራቸው ይችላል።
ቀጥታ ከፋርማሲ ወይም ካዘዘሎት አካል ውጪ የሆነን ማንኛውንም የሚዋጥ መድኃኒት አይጠቀሙ።
በኦንላይን የሚገዙ መድኃኒቶች ደህንነታቸው አስተማማኝ አይደለም።
Fentanyl ምንድን ነው?
Fentanyl ተመሳስለው የሚሰሩ ሱስ የማስያዝ ባሕሪ ያላቸው ሕገ-ወጥ መድኃኒቶች ሲሆኑ ከሌሎች ሱስ የማስያዝ ባሕሪ ካለቸው መድኃኒቶች በግምት ከ100 አጥፍ በላይ ጠንካራ ነው። Fentanyl ብዙውን ጊዜሕጋዊ ባልሆኑ የመንገድ ላይ መድኃኒቶች ባሉት ሐሰተኛ መድኃኒትና ነጭ ዱቄት ይጨመራል። Fentanyl እና ሌሎች የሱስ ማስያዝ ባሕሪ ያላቸው መድኃኒቶች ከመጠን በላይ የሆኑ መድኃኒቶች ይሆኑና ትንፋሽን በማሳጠር ለሞት መዳረግ የሚችሉ ይሆናሉ።
በየአከባበው Fentanyl የት የት ይገኛል?
በጊንግ ካውነቲ፥ Fentanyl በአብዛኛውን ጊዜ በሰማያዊ፥ በአሬንጓዴ ወይም በዳለቻ ቀለም ተመሳስለው በተሰሩት የሚዋጡ መድኃኒቶች ውስጥ ይታያል። ሌሎች ቀለሞችም ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህ መድኃኒቶች ምናልባት በ”M30″ እና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በ”K9,” “215,” እና “v48 ምልክት ይሰጣቸዋል።” Fentanyl በነጭ ዱቄት መልክም ሊሆን ይችላል።
Fentanyl በየአከባቢው በእነዚህ ነገሮች ውስጥ ይገኛል፡
የOxycodone የሚዋጡ መድኃኒቶች በየመንገዱ ይሸጣሉ ወይም ደግሞ በኢንላይን የሚገኘው Fentanyl የመኖር እድል አለው።
Fentanyl በማሽተት ወይም በመቅመስ መለየት አይችሉም። በሚዋጡ መደኃኒቶች ውስጥ Fentanyl ካለ በዓይንዎ አይቶ መናገር አይችሉም።
በአንድ ጊዜ በተመረቱት የሚዋጡ መድኃኒቶች ውስጥም እንኳ የFentanyl መጠን አንዱ ከሌላው ሊለያይ ይችላል። አንድ የሚዋጠው መድኃኒት አንድን ሰው ሳይገድለው ማነቃቃት ቢችልም፥ ሌላ የሚዋጥ መድኃኒት ደግሞ ገዳይ ሊሆን ይችላል።
ከመጠን በላይ ተወስደው ገዳይ ስለሆኑት ምን መደረግ እንዳለበት፡
ከመጠን በላይ የተወሰዱትን ወይም አነቃቂ ሕገ-ወጥ መድኃኒቶች የመጠቀም ምልክቶችን ይወቁ። አንድ ሰው የሚከተሉት ሁኔታዎች ከታዩበት ከመጠን በላይ እየወሰደ ነው ሊባል ይችላል፡
* የማይነቃ ከሆነ ወይም እነሱን ለማንቃት አስቸጋሪ ከሆነ
* ዝቅተኛ ትንፋሽ ወይም ትንፋሽ ከሌለው
* የነጣ፥ የገረጣ፥ ቀዝቃዛ የሰውነት ቆዳ ከታየበት
* ሰማያዊ ከናፍርት ወይም የጣት ጥፍሮች ከታዩበት
* ጤናማ ያልሆነ የማንኩራፋት ባሕሪ ካለው (ለምሳሌ ከፍ ብሎ የሚረብሽ ድምፅ ባለው)
* ከፍተኛ የሆነ እንቅልፍ እንቅልፍ የማለት ስሜት
ከመጠን በላይ መድኃኒቶችን የመጠቀም ምልክቶችን ካዩ ወዲያውኑ በ9-1-1 ይደውሉ።
Naloxone (Narcan)፥ በአፍንጫ የሚረጭና ሊገድል የሚችለውን ሕገ-ወጥና ሱስ የሚያስይዙ መድኃኒቶችን ከመጠን በላይ በመውሰድ የሚከሰትን ጉዳት እንደማርከሻ ሆኖ የሚያገለግልን ይስጡ። Narcanን የት ማግኘት እንደሚችሉ በstopoverdose.org ላይ ይፈልጉ።
ጥቅም ላይ ሳይውሉ የተቀመጡትን ወይም ጊዜው ያለፈባቸውን መድኃኒቶች አስወግዱ።በአከባቢዎ ድሮፕ ቦክስን በ: www.medicinereturn.org ወይም text MEDS to 667873 ያግኙ
አንድ ሰው መድኃኒትን ከመጠን በላይ ወስደዋል ብሎ ካሰቡ፥ ተመልሰው እንዲተኛ አይፍቀዱ።
ሕክምና ይሰራል
የሱስነት ባሕሪ ያላቸውን ሕገ-ወጥ መድኃኒቶችን በመጠቀም የሚከሰቱትን የጤና መቃወስ ማከምን ጨምሮ፥ በመላው ኪንጊ ካውንቲ ውስጥ ብዙ የተለያዩ የሕክምና አማራጮች አሉ።