DC Futures ምንድን ነው?
DC Futures(ዲሲ ፊዩቸርስ) ፕሮግራም ከስኮላርሺፕ በላይ ነው። ብቁ የሆኑ የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ኗሪዎች ሜጀራቸው (ዋና ኮርሳቸው) በተለዩ የፕሮግራምዓይነቶች ሆኖ ከተፈቀዱት ሶስት የአካባቢው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በአንዱ ለመማር የትምህርት ወጪውን ለመሸፈን አስፈላጊ የሆነውን እስከ $8,000 ስኮላርሺፕማግኘት ይችላሉ። ስኮላርሺፖቹን በበልግ 2022፣ ጸደይ 2023 እና በጋ 2023 ላይ መጠቀም ይቻላል። The DC Futures Program(የዲሲ ፊዩቸር) ፕሮግራምየሚከተለውን ያካትታል፣
>> >> • በ “ላስት ዶላር” የትምህርት ክፍያ እርዳታ፣ የገንዘብ ሽልማቱ በተማሪው ጥቅል የገንዘብ ድጋፍ እና በትምህርት ወጪው ላይያለውን ክፍተት ለመሙላት የታቀደ ነው።
>> >> • በዓመት እስከ $8000፣ የ DC Futures (ዲሲ ፊዩቸርስ) ፕሮግራም ተሳታፊዎች በአንድ የትምህርት ዓመት እስከ $8,000 ለማግኘት ብቁናቸው።
>> >> • የኮሌጅ ስልጠና፣ ሁሉም የ DC ተሳታፊዎች በኮሌጅ ስልጠና ፕሮግራም እንዲሳተፉ ይጠበቅባቸዋል – ይህም በ DC Futures በሚመደቡአቅራቢዎች ወይም እንደ DCPS Persists አይነት የተፈቀዱ ፕሮግራም አማካኝነት ሊሆን ይችላል። ይህ ድጋፍ ከስኮላርሺፑ በተጨማሪበዓመት እስከ $1,500 ድረስ የኪስ ክፍያ አለው።
>> >> • ተጨማሪ ገንዘቦችን ማግኘት፣ ሁሉም የ DC Futures ተሳታፊዎች በችግር ጊዜ ለሚወጡ ወጪዎች በዓመት እስከ $2,000 ያክል የድንገተኛ ጊዜገንዘብ መጠየቅ ይችላሉ። ይህ ድጋፍ አስፈላጊነት ላይ እና የገንዘብ አቅርቦት ላይ የተሞረከዘ ይሆናል።
>> >> • በየዓመቱ እንደገና ማመልከት ስለ መቻል፣ የገንዘብ ሽልማቱ ባለው የገንዘብ አቅም እና መጀመሪያ ለመጣው በቅድሚያ እንደየአመጣጣቸው የሚሰጥበመሆኑ፣ አመልካቾች በየዓመቱ የገንዘብ ድጋፉን እንደሚያገኙ ምንም ዋስትና የለም። ኗሪዎች በየዓመቱ እንደገና ማመልከት አለባቸው።
ሰለ ብቃት መስፈርቶች እና DC Futures የገንዘብ ድጋፍ ስለሚያደርግላቸው የኮሌጅ ዝርዝሮች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለውን ይመልከቱ። ለማመልከቻው እና አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች ዝርዝር በተመለከተ፣ እባክዎ የ DC Futures ድረገጽን ይጎብኙ። ለጥያቄዎች፣ የDC Futures ሰራተኞችን በosse.dcfutures@dc.gov. ያግኙ የ 2022-23 የትምህርት ዓመት የማመልከቻ ጊዜ ከፌብሩዋሪ 1፣ 2022 ላይ ነው እስከ ኦገስት 19፣ 2022 ነው። በስኮላርሺፕ፣ ለDC Futures ፕሮግራም ብቁ መሆንዎን ይመርምሩ፣ እና ከዚያ ያመልክቱ!