ይህ “እርዳታ እስኪመጣ” የተባለ በአደጋ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ፖሊስና አምቡላንስ/እሳት ማጥፊያ እስኪመጡ ድረስ መደረግ ያለባቸውን ህይወት አድን ክኽሎቶች ማስጨበጫ ትምህርት በአርሊንግተን ካውንቲ መንግስት የተዘጋጀ ስልጠና በመጪው ሐሙስ ጁን 16፣ 2022 በአካል ከ6-9፡30 pm በነጻ ይሰጣል። የትምህርት ቦታው Arlington County Fire Training Academy፣ 2800 S Taylor St፣ Arlington, VA 22006 ነው።
ይህ “እርዳታ እስኪመጣ” የተባለ ስልጠና በአገር-ዓቀፍ ደረጃ ዜጎች ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋ በሚደርስ ወቅት የትሻለ ዝግጁ እንዲሆኑና ህይወት እንዲያተርፉ የሚያበቃቸውን ክህሎት የሚያገኙበት መሰረታዊ ስልጠና ነው።
በአካል መገኘት ለማይችሉ ሰዎች ስልጠናው ኦንላይን ይገኛል። ይህን ሊንክ ተጭነው የኦንላይን ስልጠናውን መውሰድ ይችላሉ።
በአካል አርሊንግተን ካውንቲ የእሳትና አደጋዎች ስልጠና አካዳሚ ሐሙስ ጁን 16 2022 ተገኝተው መካፈል ከፈለጉ ደሞ ይህን ሊንክ ተጭነው መመዝገብ ይችላሉ።