በቂ ፈሳሽ ይጠጡ
ቢጠማዎትም ባይጠማዎትም ቀኑን ሙሉ ውሃ ይጠጡ።
ቡናና አልኮል መጠጦችን አያብዙ
መኪናዎን ከመቆለፍዎ በፊት በውስጡ ልጆችዎን፤ አዛውንት ቤተሰብዎን፤ አካል ጉዳተኛ ሰው ወይም እንስሳዎን አንዳልረሱ ያረጋግጡ። በፍፁም ሰው መኪና ውስጥ አስቀምጠው እንዳይወጡ።
ከፍተኛ ሙቀት በሚኖር ጊዜ ከቤት ውጪ ጉልበት ከሚፈልጉ ከባድ ስራዎችን ከመስራት ይታቀቡ። ግዴታ ከሆነ ደሞ አዘውትረው በጥላ ስር እረፍት ያድርጉ።
ቀለል ያሉ ልብሶችን ይልበሱ። ሰንስክሪን ይጠቀሙ። ከቤት ውጪ ሆነው ሙቀቱ ካስቸገረዎ በመንገድዎ ላይ ያሉ የገበያ ቦታዎች(ሞል)፤ የህዝብ ላይብረሪዎችና የኮሚውኒቲ ማዕከሎች ውስጥ ይግቡና ራስዎን ያቀዝቅዙ።
ራስዎን ቤተሰብዎንና ጎረቤቶችዎን በሙቀት ተጎድተው እንዳይሆን ቼክ አርጉ። እንደ መፍዘዝ፤ ማዞር፤ ማቅለሽለሽ፤ ማስታወክ፤ መውደቅ/ፌንት መንቀል/ና የጡንቻ መሸማቀቅ የሚምስሉ ስሜቶችን አስተውሉ። ነገሮች ከባሱ 911 ደውሉና እርዳታ ጥሩ።