12/12/2024
mcpd-seal-new

I-270ና I-370 መጋጠሚያ አካባቢ ወደ ደቡብ (ወደ ዲሲ) በሚወስደው አስፋልት በስተቀኝ ያሉትን ሁለት ሌኖች በ I-270 መንገድ ላይ በደረሰ 25 ፊት ገደማ ስፋት ያለው የአስፋልት መስመጥ/ሲንክ-ሆል/ ምክንያት የትራፊክ መስተጓጎል ተከስቷል። የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ እንዳስታወቀው ይህ መንገድ ተጠግኖ አገልግሎት ለመስጠት ቢያንስ እስከሰኞ ጁን 20 ጊዜ ይወስዳል።
አሽከርካሪዎች በተቻለ መጠን ተለዋጭ መንገድ እንዲጠቀሙ የካውንቲው ፖሊስ በትዊተር ገፁ መክሯል።

ይህን አደጋ ተከትሎ በራይድ-ኦን ባሶች ላይ ጊዜያዊ መስተጓጎል ተከስቷል። ይህ መስተጓጎል እስከ 2 ሳምንት ሊዘልቅ እንደሚችል ይጠበቃል።

መስተጓጎል የደረሰባቸው ባሶች ዝርዝር የራይድ-ኦን ባስ አስተዳደር በትዊተር ገፁ አስታቋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት