በዴሞክራቲክ ፓርቲ ለሞንጎምሪ ካውንቲ ኤግዚኪውቲቭ ቦታ እየተወዳደሩ ያሉ እጩዎችን ሁሉንም ለቃለመጠይቅና ለትውውቅ እንዲሁም የማህበረሠባችንን ትርታ እንዲያዳምጡ በማለት ግብዣ አድርገን እስካሁን አንድ ተወዳዳሪእኛንም ማህበረሰባችንንም አክብረው ለጥያቄዎቻችን ምላሽ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘውልናል።
ሚ/ር ኃንስ ሬይመር በቀጣይ ሳምንት ከኢትዮጲክ ባልደረባ ጋር አጭር ቆይታ ያደርጋሉ። የሞንጎምሪ ካውንቲ መራጭ ነዋሪዎች…. እኚህን እጩ ተወዳዳሪ ምን እንጠይቅልዎ። ምን ያሳስብዎታል? ቤት? ትራንስፖርት? ደህንነት? ጤና? ዩቲሊቲ? ቢዝነስ ለመጀመር ካፒታል? ጥያቄዎቻችሁን በሜሴጅ ላኩልን። እናመሰግናለን። ስለተወዳዳሪው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ሊንኩን ተከትለው ይሂዱ