አራተኛው የኮቪድ የቤት ኪራይ ድጋፍ እስከ ጁን 30 ማመልከቻዎችን ይቀበላል። ለቤት ኪራይ ድጋፍ ለማመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ። ይህን የቤት ኪራይ ድጋፍ ማመልከቻ ቅጽ ለመሙላት ድጋፍ ካስፈለገዎ የሚከተሉት ድርጅቶች ጋር መደወል ወይንም ኢሜይል ማድረግና ድጋፍ እንዲደረግልዎ መጠየቅ ይችላሉ።
- CASA : 301-431-4185
- Housing Initiative Partnership, Inc. : 301-916-5946
- Latino Economic Development Center : 202-540-7427
- Renters Alliance Inc. : info@rentersalliance.org 817-676-1548
ለጠቅላላ መረጃ ወይንም የኢቪክሽን ወረቀት ከደረሰዎ የካውንቲውን የተከራይ-አከራይ ጉዳዮች ፅ/ቤት በ311 ወይንም በ 240-777-0311 ደውለው ወይንም በ olta.intake@montgomerycountymd.gov ኢሜይል በመላክ ማናገር ይችላሉ።
በተከራይ-አከራይ ጉዳዮችና በካውንቲው ባሉ ድጋፎች ዙሪያ ካውንቲው በየጊዜው መረጃዎችን ያወጣል። ከነዚህም ፕሮግራሞች አንዱ ዛሬ ምሽት ከስር ባሉት የኢንተርኔት አድራሻዎች በቨርቿል ይከናወናል
በ Housing Initiative Partnership የተዘጋጀው ፕሮግራም ማክሰኞ ጁን 21 ከምሽቱ 7 ሰዓት ላይ ሲሆን ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው በነፃመመዝገብ ይችላሉ።
ሌላው በ Latino Economic Development Center የተዘጋጀው ፕሮግራም ማክሰኞ ጁን 21 ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ ሲሆን ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው መመዝገብ ይችላሉ።