12/12/2024
Red Simple Road Public Service Facebook Post (1)

የዲሲ ፖሊስ ከደቂቃዎች በፊት እንዳስታወቀው በኖርዝ ኢስት ዲሲ መኪና መንገድ ስቶ የርችት ማዘጋጃ ቦታ ላይ በመግባቱ በርካታ እግረኞችን ገጭቷል። ይህንን ተከትሎም ከስር የተጠቀሱትን መንገዶች ተዘግተዋል።

  • Minnesota Avenue Northeast between Sheriff Road and Hunt Place NE
  • Nannie Helen Burroughs Ave NE between Kenilworth Ave and 44th St NE

አሽከርካሪዎች ተለዋጭ መንገድ እንዲፈልጉ ተመክሯል።

ባለስልጣናቱ አደጋው ከባድ እንደሆነና ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት በቦታው እየተዘጋጁ እንደሆነ በትዊተር ገፃቸው አስታውቀዋል።

ፖሊስ ከደቂቃዎች በፊት በትዊተር ገፁ እንዳስታወቀው ሁለት ሰዎች እዛው የአደጋው ቦታ ላይ ለህልፈት ተዳርገዋል። ፖሊስ አሁንም በምርመራ ላይ እንደሆነ አስታውቋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት