የሞንጎምሪ ካውንቲ እሳትና ሌሎች አደጋዎች ተከላካይ መስሪያ ቤት በቀጣይ አመት ሊያደርገው ላሰበው ቅጥር እጩ ምልመላ ጀምሯል። ይህ ለ26 ሳምንት የሚቆይ የእጩዎች ስልጠና በመጭው አመት ጁላይ 2023 ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።
መስሪያ ቤቱ በስራ ማስታወቂያው እንዳሰፈረው ከ1 በላይ ቋንቋ ተናጋሪዎች የበለጠ እንደሚፈልጉና አማርኛ ቋንቋም ከሚፈለጉት አንዱ እንደሆነ አስታውቋል።
በዚህ ስራ ላይ ለመቀጠር ከእንግሊዝኛ ቋንቋ በተጨማሪ የአሜሪካዊ ዜግነት ወይንም ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ (ግሪን ካርድ) ያስፈልጋል። አመልካቾች የፅሁፍ ፈተና የሚፈተኑ ሲሆን በተጨማሪም የአካል ብቃት ፈተናዎችን ማለፍ ይጠበቅባቸዋል።
ፈተናዎቹን አልፈ ለቅጥር የሚበቁ እጩዎች ከ55,175.00 እስከ 89,322.00 አመታዊ ደሞዝ ይከፈላቸዋል።
ለማመልከት ይህን ተከትለው ይሂዱ።